Logo
YenetaTube
ቅዱስ ዑራኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ🙏

በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ🙏

መልአከ ብርሃናት፣ ለሚጠሩት ፈጥኖ የሚደርስ መሆኑን የቤተ ክርስቲያናችን መጻሕፍት በስፋት ይገልጹታል፡፡ ከሰባቱ ሊቃነ መላዕክት አንዱ ሲሆን በየዓመቱ ጥር 22 በዓለ ሲመቱ ይከበራል፡፡ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ዑራኤል፡፡ የስሙን ትርጓሜ ሊቃውተ ቤተክርስቲያን ሲያስቀምጡም “ዑራ” ማለት ብርሃን ማለት ሲሆን “ኤል” አምላክ ማለት ነው፡፡ በዚህም ዑራኤል ማለት የአምላክ ብርሃን፣ ወይም የብርሃን ጌታ ማለት ነው፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር በመባርቅትና በነጎድጓድ ላይ የተሾመው ታላቅ መልአክም ነው ቅዱስ ዑራኤል፡፡ በመጽሐፈ ሔኖክ 6÷2 መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ይሰማራል።

ምሥጢረ ሰማይና እውቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለትም የፀሐይን፣ የጨረቃን፣ የከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለነቢዩ ሄኖክ ነግሮታል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብጽ ስትሰደድ መንገድ የመራ፣ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ በተሰቀለ ጊዜ ክቡር ደሙን በብርሃን ጽዋ ተቀብሎ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨ እርሱ ነው፡፡ ሊቀ መልአኩ የጌታችንን ደም የረጨበት ጽዋ በሀገራችን በኢትዮጵያ እመጓ ቅዱስ ኡራኤል እንደሚገኝ ስፍረዋን የጎበኙ ጸሐፍትና የስፍራው አገልጋዮች ይገልጻሉ፡፡

ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ጽዋ ጥበብን ያጠጣ፣ ኢትዮጵያዊውን ሊቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በርካታ ቅዱሳት መጻሕፍትን አንዲደርሱ ያገዘ፣ የረዳና የዕውቀት ጽዋን ያጠጣ መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ነው፡፡ በርካታ ቅዱሳን አባቶች ምስጢር እንዲገለጥላቸው የረዳቸው ቅዱስ ዑራኤል መሆኑ በበርካታ የቤተ ክርስቲያናችን መጻሕፍት ሰፍሮ ይገኛል፡፡ አፋቸውን ከፍተው የምስጋና ቃል እንዲናገሩ፣ የሚጽፉበት ብዕር በመንፈስ ቅዱስ የተቃኘ ለሕይወት ድህነት የሚሆን መልዕክት እንዲያስተላልፍ ቅዱስ ዑራኤል አግዟቸዋል፡፡ ይህም ምሥጢር ማናገር የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ቢሆንም የተሠወረውን መግለጥ፣ በአዲስ ቋንቋ ማናገር ለመላእክት የተሰጠ ጸጋቸው መሆኑም ያሳየናል፡፡

ዛሬም በየገዳማቱ ያሉ ቅዱሳን አባቶችና እናቶች ዓለምን ንቀው፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ጤዛ ልሰው፤ ግርማ ሌሊቱን፣ ድምጸ አራዊቱን፣ ጸብአ አጋንንቱን ተቋቁመው በጾምና በጸሎት ሲተጉ ይህ ቅዱስ መልአክ ዑራኤል ፈጽሞ ይራዳቸዋል፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በራዕይ 8÷4 “የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ።” እንዲል በገዳማውያኑ መካከል ተገኝቶ ጸሎታቸውን ያሳርጋል፤ ልመናቸውን በአምላክ ፊት ያቀርባል፡፡ ቅዱሳን መካናትን ስናግዝ፣ ገዳማትን ስንረዳ፣ በዓታቸውን ስናጸና የገዳማውያኑ ጸሎትና በረከት ይደርሰናል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

1000766349227

ወይም

አቢሲንያ ባንክ

262281132

የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921

4 days ago
Administrator
4 days ago
Replying to YenetaTube 's post

Administrator sent a gift to YenetaTube

10$