Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) መስከረም 17፣ 2019 ዓ.ም (Sept 27, 2026)፣ ልዑል ኤርምያስ ሣህለ ሥላሴ እና ልጃቸው ልዑል ሩፋኤል ኤርምያስ፣ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ እ.ኤ.አ. በ1954 በነበራቸው የመጀመሪያ የአሜሪካ መንግስታዊ ጉብኝት ወቅት በተገኙበት በታሪካዊው "አቢሲኒያ ባፕቲስት ቤተክርስቲያን" በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

አጼ ኃይለ ሥላሴ በወቅቱ ቤተክርስቲያኗን የጎበኙት ከልዑል ኤርምያስ አባት (ከታናሽ ልጃቸው) ልዑል ሣህለ ሥላሴ ጋር ነበር። የኒውዮርክ ሃርለም ማህበረሰብ እና ቤተክርስቲያኗ በፋሺስት ጣሊያን ወረራ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም ላሳዩት ታሪካዊ አጋርነት ምስጋና ለማቅረብም፣ ንጉሰ ነገሥቱ እጅግ ማራኪ የሆነ የዑደት መስቀል ለቤተክርስቲያኗ መጋቢ ለነበሩት ቄስ አዳም ክሌይተን ፓውል (በኋላ ታዋቂ የኮንግረስ አባል ለሆኑት) በስጦታ አበርክተው ነበር።

በአጋጣሚ ሆኖ ይህ ታሪካዊ የብር መስቀል የተሰራው በቤተ መንግሥቱ የጌጣጌጥ ስራ ባለሙያዎች በነበሩት አቶ ደጀኔ በላይነህ እና አቶ ሽፈራው በላይነህ (የአሁኑ የዘውድ ምክር ቤት /RET/ ቦርድ ፕሬዚዳንት የሰለሞን ክብሬ አያቶች) እጅ ሲሆን፣ መስቀሉ ዛሬም ድረስ በቤተክርስቲያኗ በክብር ተቀምጦ የቤተክርስቲያኗ መለያ አርማ ሆኖ ያገለግላል።

ከ72 ዓመታት በኋላ የአያታቸውን እና የአባታቸውን ፈለግ በመከተል በሃርለም በሚገኘው በዚህ ታሪካዊ ቤተክርስቲያን የተገኙት ልዑል ኤርምያስ እና ልጃቸው ልዑል ሩፋኤል፣ በቤተክርስቲያኑ ምዕመናን እና አስተዳደር እጅግ ደማቅ እና የተከበረ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ይህ ጉብኝት በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ ጥቁር ማህበረሰብ መካከል ያለውን የረዥም ጊዜ የትግል እና የድል ታሪካዊ ትስስር ዳግም ያደሰ ክስተት ሆኖ አልፏል።

5 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.