የአሽከርካሪዎችን ዕገታ ለማስቆም ከመንግሥት ጋር እየሠራ እንደሆነ የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሠሪዎች ፌዴሬሽን አስታወቀ
በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በአሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰውን ዕገታ ለማስቀረት እና ጤናማ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት እየተሠራ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ትራንስፖርት አሠሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃኔ ዘሩ ለአሐዱ ሬድዮ እንዳስታወቁት፣ በ2019 የበጀት ዓመት ችግሩን ለማቃለል ፌዴሬሽኑ ከመንግሥት ጋር በጥምረት እየሠራ ነው።
በወለንጭቲ፣ በአሊዶሮ፣ በጎንደርና በተለያዩ አካባቢዎች ትጥቅ ያነሱ አካላት በመኖራቸው በአሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰው ዕገታ በጊዜ ሂደት እንዲቆም ይደረጋል ብለዋል።
ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ፣ አሽከርካሪዎች ፈተናዎችን ተቋቁመው አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ዕገታው ሙሉ በሙሉ አለመቆሙን የጠቆሙት አቶ ብርሃኔ፣ በቀጣይም የችግሩን አሳሳቢነት በማየት ፌዴሬሽኑ ከሌሎች ተቋማት ጋር ለመሥራት ማቀዱን ገልጸዋል።
በተመስገን ተጋፋው
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

7 days ago