የግሪክ የጥገኛነት ህግ ማሻሻያ
#ethiopia | የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ (UNHCR) ግሪክ የጥገኝነት ማመልከቻዎችን ለማገድ ባቀረበችዉ የሕግ ማሻሻያ ላይ ከፍተኛ ስጋት እንዳለው ገለጸ፡፡
ይህ ማሻሻያ ከሰሜን አፍሪካ በጀልባ የሚገቡትን ስደተኞች የጥገኝነት ማመልከቻዎችን ለሶስት ወራት የሚያግድ ሲሆን ብሎም ስደተኞች ሳይመዘገቡ ወደመጡበት እንዲመለሱ የሚያደርግ አሰራር መሆኑ ተነግሯል፡፡
“ጥገኝነት መጠየቅ በአለም አቀፍ በአውሮፓ እና በአገር ውስጥ ሕጎች የተደነገገ መሰረታዊ የሰብአዊ መብት መሆኑን በመግለጽ ይህ መብት ሰው እንዴትም አድርጎ ወይም የትም ሀገር ቢደርስ ለሁሉም ይሰራል” ሲል ነው ኤጀንሲው ያሳሰበው፡፡
ኤጀንሲው አክሎም ሰዎችን ሕይወታቸውን ወይም ነጻነታቸውን አደጋ ላይ ወደሚወድቅበት ቦታ መመለስ “የአለመባረር መርህ”ን መጣስ እንደሆነ አስጠንቅቋል::
“ሀገራትም ከዚህ ጠቃሚ የአለም አቀፍ ሕግ መርህ መዛባት አይችሉም” ብሏል፡፡
UNHCR በጋቭዶስ እና ክሬት ደሴቶች ላይ በቅርቡ የመጡ ስደተኞች ያስከተሉትን ጫና የሚያውቅ ቢሆንም ”የሀገርን ድንበር መቆጣጠር ከአለም አቀፍ እና ከአውሮፓ ሕጎች ጋር መስማማት አለበት”ብሏል፡፡
ኤጀንሲው በአውሮፓ ህብረት ውስጥ እንደ ግሪክ ያሉ ሀገራትን ለመደገፍ ጠንካራ የአንድነት እና ሀላፊነትን የመጋራት እርምጃዎችን መውሰድ ያስፈልጋል ብሏል፡፡ #nbc_ethiopia

1 year ago