Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የሙዚቃ አቀናባሪዎችንና ዲጄዎችን ጨምሮ ዘመናዊ የኪነጥበብ ባለሙያዎችን የሚሸልም አዋርድ ተዘጋጀ፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ የፈጠራ ጥበባት አዲስ ገፅታ›› በሚል መርህ በአይነቱ አዲስ የሆነ የዘመናዊ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ሽልማት መዘጋጀቱ ተገለፀ፡፡

አደይ ኮንቴምፖራሪ አርት አዋርድ የተሰኘ መጠሪያ ያለው ይህ ሽልማት የፊታችን ጥቅምት 7 ቀን 2019 በአዲስ አበባ አድዋ መታሰቢያ ሙዚየም እንደሚከናወን አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡ የአዋርዱ ሀሳብ አመንጪ ታዋቂው የሰርከስ ባለሙያና ዳይሬክተር አርቲስት ተክሉ አሻግር(ሄኖክ) እንደገለፀው በጂ ኤይት ኢንተርቴይመንትና በኢተርናል ሚዲያ ኮምንኬሽን ዋና አጋርነት ሽልማቱ ከዘንድሮ አንስቶ በየአመቱ መስከረም ወር የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የአዋርዱን አላማ ሲገልፅም ‹‹በአገራችን የኮንቴምፖራሪ አርቲስቶችን እውቅና ለመስጠት፣ ክንውን ጥበባቶችን በኤግዝቪሽንና በመድረክ ደረጃቸውን ጠብቀው ለማቅረብ እንዲሁም የጥበቡ ባለሞየዎች እርስ በእርስ የሚገናኙበት የሚደጋገፉበትና አገራችን እየተፈጠረ ላለው ገበያ እድሎች እራሳቸውን የሚያስተዋወቁበት መድረክ እንዲሆን በማሰብ ነው፡፡›› ብሏል፡፡

በዘንድሮው በዘንድሮው የመጀመርያው አደይ ኮንቴምፖራሪ አርት አዋርድ በስድስት ኪነ-ጥበባት ትዕይንታዊ ክንውን ዘርፎች ለ19 የጥበቡ ፈጠራ ባለሞያዎችና የህይወት ዘመን ተሸላሚዎች እውቅና እንደሚሰጥም አስረድቷል፡፡ እነዚህ ዘርፎችም በኮንቴምፖራሪ ሙዚቃ ዘርፍ የሙዚቃ አቀናባሪዎችንና ዲጄዎችን የሚያካትቱ ሲሆን በኮንቴምፖራሪ ዳንስ ዘርፍ የአመቱ ምርጥ የወንድና ሴት ዳንሰኞችን፣ እንዲሁም የአመቱ ምርጥ ሰአሊዎችን፣ የአመቱ ምርጥ የሰርከስ ባለሙያዎችንና ሌሎችንም የሚያካትቱ ናቸው፡፡

ለሽልማቱ እጩዎችን የመምረጥ ሂደቱ ተጠናቆ ከዛሬ አንስቶ በአዋርዱ ድረ ገፅ ላይ ድምፅ የመስጠት ሂደት እንደሚጀመር የጠቆመው አርቲስት ሄኖክ የህዝብ ምርጫ 60 ፐርሰንት ድምፅ እንደሚኖረውና 40 ፐርሰንት የሚሆነውን ድምፅ የሚሰጡት በየዘርፉ የተሰየሙ አንጋፋና በሞያና ስነ- ምግባራቸው የተመሰገኑ ጥበበኞች መሆናቸውን አስታውቋል፡፡ የዚህ ሽልማት ስነስርአት በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ቴሌቪዥን በቀጥታ እንደሚሰራጭም ተናግሯል፡፡

7 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.