ባህር ዳር ምን ታሳይን ይሆን?
ጁን 9 2022 ከአራት ቀናት በፊት ማላዊ ድረስ ሄዶ የ2 ለ 1 ሽንፈት አስተናግዶ የነበረው ብሔራዊ ቡድናችን በጉዳት ምክንያት እነ ሞሃመድ ሳላህን ከስብስብ ውጪ ካደረገችው ግብፅ ጋር ጨዋታውን አደረገ። ልክ እንደ ዛሬው የሴኔጋል ጨዋታ ሁሉ—ባለፈው በሱዳን እንደተሸነፈችው—በወቅቱም ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ አብዛኛው ዓለም "ኢትዮጵያ የለመደችውን ሽንፈት ትቀምሳለች፤ ግብፅ ግብፅ ናት" ብለው ነበር የጠበቁት። ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በምድቡ ሁለተኛ ጨዋታ ግብፅ ከኢትዮጵያ ሲገናኙ ማንም ያልጠበቃት ሀገራችን የመጀመሪያ ግቧን በአንበሳው ዳዋ ሆቴሳ አማካኝነት ገና ጨዋታው እንደጀመረ በ20ኛው ደቂቃ ላይ አገኘች።
ደቂቃዎች ነጎዱ ዓለም ገና ከአሁኑ "ኢትዮጵያ ካገባች መስራውያን ውጤቱን ለመቀልበስ ይሰራሉ አለ። እነ ኡመር ማርሙሽ፣ ዚዞ እና ሞሃመድ ሙስጠፋን የመሳሰሉ ግብፃውያንን ስም እያነሱ "ኢትዮጵያ ተስፋ ቁረጪ፣ አንድ ጎል አያስተማምንም" እያሉ የሚሳለቁ አልጠፉም ነበር። ነገሩ ግን ፍጹም ሌላ ሆነ! ዓለም "ግብፅ ከመቼ ጀምሮ ቢጫ እና አረንጓዴ መለያ ማድረግ ጀመረች?" እያሉ እስኪገረሙ ድረስ ዋልያዎቹ ግብፅን በሜዳ ላይ መጫን ቀጠሉ።
ዓለም የቱ ግብፅ የቱስ ኢትዮጵያ እንደሆነ ግራ ተጋብቶ እያየ 30 ደቂቃዎችን ተሻገርን፤ አምበሉ ሽመልስ በቀለ ኢትዮጵያን በሁለት ግብ ልዩነት እንድትመራ አደረጋት። አሁንም የዓለም እግር ኳስ አፍቃሪ በነገሩ ተገርሟል በዕለቱ ዕድለኛ ያልነበረው ብሔራዊ ቡድናችን ጨዋታውን በሁለት ጎሎች ብቻ አጠናቀቀ አቡበከር ናስር ያለቀላቸውን ኳሶች ባያመክን እንዲሁም ሌላ ግብ በኦፍሳይድ ምክንያት ባይሻር ኖሮ ሀገራችን ግብፅን ታሪካዊ ውርደት አከናንባት ነበር።
ታዲያ ያ ታሪክ ዛሬስ ይደገም ይሆን? ዛሬ ማክሰኞ በባህር ዳር ስታዲየም ከሴኔጋል ጋር በምናደርገው ፍልሚያ ምን እናይ ይሆን?
ዋልያዎቹ የ2022ቱን ተአምር ደግመው አፍሪካን የሚያስደምሙበት ምሽት እንዲሆን ምኞታችን ነው።
ግብፅን በምድብ ሁለተኛ ጨዋታ ስንገጥም ኮከባቸው ሳላህ አልነበረም!
ሴኔጋልን ዛሬ በምድብ ሁለተኛ ጨዋታ ስናገኛት ኮከቦቻቸው ማኔና ሳር የሉም!👀
@Bisrat_sport_433et

7 days ago