በዘመናዊ የኪነ ጥበብ ፈጠራ ላይ ያሉ ወጣቶችን ለማበረታታት እና አለም አቀፍ የስራ ዕድል ለመፍጠር ያለመ አዋርድ ሊካሄድ ነዉ
ጂ ኤይት ኢንተርቴይመንት እና ፕሮሞሽን ከኢተርናል ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ጋር በመተባበር የወጣቶችን የዘመናዊ ኪነ ጥበብ አቅምና ፈጠራ ለማበረታታት ያለመ "አደይ ኮንቴምፖራሪ አርት አዋርድ" ሊያካሄድ መሆኑን አስታዉቋል ።
በሌላው ዓለም ለጥበብ ሥራ የሚሰጠው እውቅና ከፍተኛ ቢሆንም በሀገራችን ግን በዘመናዊ የኪነጥበብ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ወጣቶችና የፈጠራ ባለሙያዎች የሚገባቸውን ያህል እውቅና እያገኙ እንዳልሆነ ተገልጿል።
በጂ ኤይት ኢንተርቴይመንት እና ፕሮሞሽን የተዘጋጀዉም ይህ አዋርድ ኮንቴምፖራሪ ሙዚቃ ፣ዳንስ ፣ፋሽን ፣ሰርከስ ፣ስዕል እንዲሁም አጫጭር ፊልሞች እና ሌሎችንም ጨምሮ 19 የሚሆኑ የሽልማት ምድቦችን መካተቱን የጂ ኤይት ኢንተርቴይመንት እና ፕሮሞሽን ዋና ስራ አስፈፃሚና አርቲስቲክስ ዳይሬክተር አቶ ተክሉ አሻግሮ (ሔኖክ ) መናገራቸዉን ብስራት ሬዲዮ ሠምቷል ።
አዋርዱ ጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም የሚካሄድ ሲሆን በዕለቱም የስዕልና ቅርፃ ቅርፅ ኤግዚቢሽን፣ ከሰርከስና ዳንስ የተዋሃዱ ኮንቴምፖራሪ ትርዒቶች፣ የፋሽን ሾውና የዘመናዊ ሙዚቃ ስራዎች በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅተው ይቀርባሉ ተብሏል ።አዋርዱ ለወጣት ባለሙያዎች እውቅና ከመስጠት ባለፈ ሥራዎቻቸውን ለአለም አቀፍ ገበያ በማስተዋወቅ የሥራ ዕድል የመፍጠር ዓላማ እንዳለው ተጠቁሟል። ማህበረሰቡም ለእጩዎቹ በዌብ ሳይት እና ቴሌግራም ቦት ድምፅ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል ።
የእጩዎቹ ጥቆማ ሂደት መጠናቀቁ አዘጋጆቹ የገለፁ ሲሆን የተመረጡ ዕጩዎችን በአዋርዱ ድረ ገፅ ላይ በማስተዋወቅ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱን እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል ። የአሸናፊዎቹ ምርጫ 60 በመቶ በህዝብ ድምፅ እና 40 በመቶ ደግሞ በዳኞች የሚሰጥ መሆኑን ብስራት ሬዲዮ ሠምቷል ።
በመባ ወርቅነህ #ዳጉ_ጆርናል

9 days ago