የመደመር መንግሥት ታላቅ ራእይ፦ ጠንካራ ተቋማትና የማትበገር ኢትዮጵያን መገንባት
*********************
ሀገር መገንባት በጥቂት ዓመታት የሚጠናቀቅ ስራ ሳይሆን ትውልዶች የሚፈፅሙት ታላቅ ጉዞ ነው፤ ኢትዮጵያም ዛሬ በዚህ የዘመናት የታሪክ ምእራፍ ውስጥ ትገኛለች።
የሀገራችን የወደፊት አቅጣጫ የሚወስኑ ወቅታዊ የፖለቲካ የማህበራዊ እና የኢኮኖሚ ፈተናዎችን ወደ ተቋማዊ መፍትሄ ለማሸጋገር የሚደረገው ጥረት የሀገረ መንግስት ግንባታን በጠንካራ መሰረት ላይ የመጣል አስፈላጊነትን አጉልቶ አሳይቷል።
የመደመር መንግስትም ጊዜያዊ ስኬትን ብቻ ሳይሆን ለዘመናት የሚፀና ሀገረ መንግስት የመገንባት ራእይ ይዞ ተነስቷል።
ይህ የሀገረ መንግስት ግንባታ ራእይ በሶስት ዋና ዋና ምሰሶዎች ላይ መልህቁን የጣለ ነው፡፡ የመጀመሪያው ምሰሶ የፀና ሀገረ መንግስት ግንባታ ሲሆን በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በርካታ ፈተናዎች ባሉበት ሁኔታ እንኳ ዜጎቿ በነቂስ ወጥተው ድምፃቸውን የሰጡበትን ነፃ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ጠቅላላ ምርጫ በስኬት አጠናቃለች።
ምርጫ የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ማጠናከሪያ በመሆኑ ይህ እርምጃ ትልቅ ስኬት ነው፡፡ ጠንካራ ሀገር የሚገነባው ደግሞ በጠንካራ ተቋማት ብቻ በመሆኑ እንደ ምርጫ ቦርድ፣ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ የፍትህና የፀጥታ ተቋማት እንደ አዲስ ተደራጅተው በስኬት ጎዳና ላይ ይገኛሉ።
ሁለተኛው ምሰሶ የማትበገር ሀገር መገንባት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ስርአቶችና መንግስታት ቢያልፉም ተቋማት ሲጠነክሩ ሀገር መሻገሯ አይቀሬ ነው። በመሆኑም ዛሬ የሚገነቡት ተቋማትና ሀሳቦች ሀገርን ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚያሸጋግሩ ናቸው።
ሶስተኛው ምሰሶ የብልፅግና ተምሳሌትነት ሲሆን የትናንትናውን ታሪካዊ ቅርስ በማደስ የዛሬውን ትውልድ በማነቃቃትና ነገንም በማሻገር የትውልድ ተከታታይነት በተግባር እየተረጋገጠ ይገኛል።
ከዚህ ሁሉ በላይ ግን የኢትዮጵያ ህዝቦች ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምእራብ በጥልቅ የተሳሰረ ማንነት የሚያጋሩ መሆናቸው ዋናው መሰረት ነው አንዳንዶች ልዩነትን ለመዝራት ቢሞክሩም አብሮነቱ ከጥንት ጀምሮ የነበረና የጋራ ሀገር የመገንባት ፍላጎት ውጤት ነው።
በስኬት የጠናቀቀዉም ሀገራዊ የምክክር ሂደትም የዘመናት የታሪክ ስብራቶችን በመጠገን ብሄራዊ መግባባትን ለመፍጠር ከፍተኛ ሚናን ተጫዉቷል።
ይህ ያልተቋረጠ ርብርብ የሚያስፈልገው የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ከተራ የአስተዳደር መዋቅር ማጠናከር ባለፈ በመንግስትና በዜጎች መካከል አዲስ "ማህበራዊ ውል" የሚፈጥር ነው።
በዚህ ማእቀፍ ውስጥ መንግስት የህግ የበላይነትን ፍትህ የሰላምንና የልማት እድሎችን የማረጋገጥ ሀላፊነት ሲወስድ ዜጎች ደግሞ ተመልካች ሳይሆኑ ባለቤት በመሆን ህግን በማክበርና የሀገራዊ ጥቅምን በማስቀደም ይሳተፋሉ።
ዘላቂ ሰላምና የኢኮኖሚ ጥንካሬ ከዚህ የጋራ ባለቤትነት ጋር በቀጥታ የተሳሰሩ በመሆናቸው አዲሱ ማህበራዊ ውል የዛሬን ፈተናዎች ከመመለስ አልፎ ለቀጣይ ትውልድ የሚሻገር ተቋማዊና ማህበራዊ መሰረት የሚጥል ይሆናል።
በብሌን ደምበሎ

8 days ago