Logo
YeneTube
ካለፈው ሳምንት ማክሰኞ መስከረም 12 እስከ አርብ መስከረም 15፤ 2019 ድረስ ባሉት ቀናት፤ የኮረም እና አላማጣ ሆስፒታሎች ከ420 በላይ የጦርነት ቆስለኞችን መቀበላቸውን ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን (MSF) አስታወቀ።

በሰሜን ምዕራብ ትግራይ፣ ሽረ ከተማ በሚገኘው ስሁል ሆስፒታል፤ ባለፈው አርብ ብቻ ከ300 በላይ በጦርነት የቆሰሉ ግለሰቦች መድረሳቸውንም ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ገልጿል።

ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን ዛሬ ሰኞ መስከረም 18፤ 2019 ባወጣው መግለጫ፤ አሁን ባለው “ወቅታዊ ሁኔታ” ምክንያት የአላማጣ ሆስፒታል እንቅስቃሴዎች መቋረጣቸውን ይፋ አድርጓል።

በዚሁ አካባቢ በጸጥታ ምክንያት የማህበረሰብ አገልግሎትም መቋረጡን ድርጅቱ አመልክቷል።

የግብረ ሰናይ ድርጅቱ “በጦርነት የቆሰሉ ሰዎች በከፍተኛ ሁኔታ መጨመራቸውን ተመልክቼባቸዋለሁ” ባላቸው ሆስፒታሎች፤ ሰራተኞቹን ተጨማሪ ድጋፍ እንዲሰጡ ማሰማራቱን አስገንዝቧል።

ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን በዛሬው መግለጫው፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ባሉት ግጭቶች ምክንያት “ቁጥራቸው እየጨመረ መጥቷል” ላላቸው ታካሚዎች የሚያስፈልጉ ድጋፎችን ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ እያቀረበ መሆኑንም ጠቁሟል።

🔴ለዝርዝሩ ➡️ https://ethiopiainsider.co...

EthiopiaInsiderNews
10 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.