Logo
Getu Temesgen
በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያዊያን ስጋት ላይ ወድቀዋል!
#ethiopia | በደቡብ አፍሪካ የመስከረም 30 የጊዜ ገደብ እየቀረበ ሲመጣ በሀገሪቱ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ ፍርሃት እና ድንጋጤ ነግሷል።

"March and March" የተሰኘው የፀረ-ስደተኞች እንቅስቃሴ ቡድን በስደተኞች ላይ ስጋት ፈጥሯል።

ቡድኑ ህገ-ወጥ ስደተኞች እስከ መስከረም 30 ድረስ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቂያ ሰጥቷል።

ቡድኑ የሰጠው ማስጠንቀቂያ ተከትሎ በደርባን ጆሃንስበርግ ፕሪቶሪያ እና ኬፕታውን ባሉ ትልልቅ ከተሞች በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ቀጥተኛ ስጋት ደቅኗል።

ከዚህ ቀደም በነበሩ ተመሳሳይ የፀረ-ስደተኞች የተቃውሞ ሰልፎች ወቅት የኢትዮጵያውያን ሱቆች ተዘርፈዋል ተቃጥለዋል፤ የሰው ህይወትም አልፏል።

የደቡብ አፍሪካ መንግስት እና ፖሊስ እንደዚህ አይነት መደበኛ ያልሆኑ የጊዜ ገደቦች የህግ መሰረት የላቸውም ሲሉ አሳውቀዋል።

ፖሊስ ማንኛውም አካል በራሱ ህግ ማበጀት እንደማይችል እና ጥቃት የሚያደርሱ አካላትን በህግ እንደሚጠይቅ ገልጿል።

ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳም በስደተኞች ላይ የሚደረጉ ጥቃቶችና እና ንግግሮችን ኮንነዋል።

በአሁኑ ሰዓት በብዙ ከተሞች ያሉ ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎች መኖሪያ እና ሱቃቸውን በመዝጋት በጥንቃቄ ሁኔታውን እየተከታተሉ ይገኛሉ ተብሏል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #southafrica #ethiopiansinsouthafrica #durban #johannesburg #pretoria

10 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.