Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአዲስ አበባ ታላቅ የቦክስ ውድድር ሊካሄድ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አድዋ መታሰቢያ ሙዚየም የፊታችን አርብ ታላቅ የቦክስ ግጥሚያ እንደሚከናወን አዘጋጆቹ ገለፁ፡፡ በውድድሩ ላይ ከፌዴራልና ከኦሮሚያ ክልል ክለቦች የተውጣጡ 16 ቦክሰኞች ከ48 እስከ 80 ኪሎ ባለው ዘርፍ እንደሚፋለሙም አስታውቀዋል፡፡

በእለቱ 8 ውድድርች እንደሚካሄዱ ጠቅሰውም ከእነዚህ ውስጥ 7ቱ የወንዶችና አንደኛው በሴቶች መካከል የሚከናወን ፍልሚያ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ከአዘጋጆቹ አንዱ የሆነው የአፍሮኮ ስራ አስኪያጅ አቶ ኦብሳ አብዲሳ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በ57 ኪሎ ግራም በፌዴራል ፖሊሱ ተወዳዳሪ ኮንስታብል ሳምሶን ጌታቸውና በዩናይትድ ስዊት ቦክስ ክለብ ተወዳዳሪው አቡበከር አብዱልቃድር መካከል የሚካሄደው ዋና የእለቱ ፍልሚያ ይሆናል፡፡

በ80 ኪሎ ግራም ደግመ በፌዴራል ማረሚያ ቤቱ ማሞ ሞሲሳና በዩናይትድ ክለቡ በረከት ግሮ መካከል የሚከናወነው ግጥሚያ ዋና እንደሚሆን ጠቅሰው አሸናፊዎቹ ቀበቶ እንደሚሸለሙ አስታውቀዋል፡፡ በሴቶች ደግሞ የድሬደዋ ከነማዎቹ ነጌኛ ታደሰና ወርቅነሽ ዋቅጅራ የሚገናኙ ይሆናል፡፡ ወርቅነሽ በአውሮፓ በተካሄደ የአለም ሻምፒዮና ለኢትዮጵያ ተሳትፋ ዲፕሎማ ያስገኘች ሲሆን ሁለቱ ሴቶች ከሳምንት በኋላ በኬንያ በሚከናወነው የአፍሪካ ቦክስ ውድድር የሚሳተፉ ናቸው፡፡

የኤችኬ ኢንተርቴይመንት ስራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ ታዬ እንደተናገሩት ይህ ውድድር በኢሬቻ በአል ዋዜማ የሚከናወን በመሆኑ ‹‹ኢሬቻ ግራንድ ፋይት›› የሚል መጠሪያ የሚኖረው ነው፡፡ ውድድሩን አፍሮኮ ትሬዲንግና ኤች ኬ ኢንተርቴይመንት ከአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር ያዘጋጁት ሲሆን አርብ 2 ሰአት የሚጀምረው ውድድር ከለሊቱ 6 ሰአት እንደሚጠናቀቅ ገልፀዋል፡፡ ተመልካቾች የመግቢያ ትኬቱን በአዋሽ ባንክ በኩል የሚገዙበት ሁኔታ መመቻቸቱን አቶ ሀብታሙ ጨምረው አስታውቀዋል፡፡

8 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.