Logo
SeledaPost
ተመሳሳይ ፆታ ያላቸው ሰዎች በአንድ መታጠቢያ ክፍል ውስጥ መግባት እንደማይችሉ የፍልወሃ አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ።

ከወቅቱ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ሰዎች ወንድና ወንድ ወይም ሴትና ሴት ሆነው በአንድ መታጠቢያ ክፍል ውስጥ መግባት እና  አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉ የፍልወሃ አገልግሎት ለብስራት ሬድዮ አስታውቋል።

የተቋሙ የገበያ ጥናት አገልግሎት ዳይሬክተር  ወ/ሮ ኢትዮጵያ አብረሃም ከብስራት ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት በአንድ ወር  ውስጥ 150 ሺህ ሰዎች የፍል ውሀ አገልግሎትን  የሚጠቀሙ ሲሆን በዓመት 1.8 ሚሊዮን የሚጠጉ ደንበኞችን ተቋሙ እንደሚያስተናግድም ነው የገለፁት።

ወይዘሮ ኢትዮጵያ አክለው እንደገለፁት አቅመ ደካማ አባትን ወይም እናትን ለመርዳት አብሮ መግባት ሲያስፈልግ ማንነትን የሚገልፅ መታወቂያ በመጠየቅ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ይደረጋል ያሉ ሲሆን ወጣቶች እህትማማቾችም ቢሆኑ እንኳን በተለያዩ ክፍሎች ውስጥ ገብተው እንዲታጠቡ እንደሚያደርግ አገልግሎቱ ገልጿል።

አያይዞም ደንበኞች ቅሬታቸውን የሚያቀርቡበት የቅሬታ መስጫ ሳጥን እና መዝገብያ መዘጋጀቱን የገለጹ ሲሆን፣ ቅሬታዎቹ በየጊዜው እየተነበቡ ማስተካከያዎች ይደረግባቸዋልምብሏል።

Seledadotio
Seledadotio
9 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.