Logo
YeneTube
የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ክፍያ በባንኮች ላይ አዲስ ውጥረት ፈጠረ

​የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓትን (ፋይዳ) የሚያስተዳድረው የመንግሥት ልማት ድርጅት "ፋይዳቨርስ" ( ፣ ቀደም ሲል በነጻ ይሰጥ የነበረውን የመታወቂያና ባዮሜትሪክ ማረጋገጫ አገልግሎት ለንግድ ባንኮች በክፍያ ማቅረብ መጀመሩ በባንኮች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን አስነስቷል።

​በቀረበው የፋይዳቨርስ የታሪፍ ረቂቅ መሠረት፣ ባንኮች ለአንድ ሰው መረጃ እስከ 20 ብር የሚያስከፍሉ አገልግሎቶችን እንዲጠቀሙ ታቅዷል።

የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር የታሪፉ መጠን ከፍተኛ መሆኑንና ያለ ውይይት የተጣለ ነው በማለት ተቃውሞውን አቅርቧል።

በተጨማሪም ውሉ ባንኮች ይህንን ወጪ ወደ ደንበኞች እንዳያስተላልፉ የሚከለክል በመሆኑና አገልግሎቱ ባልተሳካላቸው ሙከራዎች ላይ እንኳ ክፍያ የሚጠይቅ በመሆኑ ቅሬታውን አጠናክሮታል፡

​ፋይዳቨርስ በበኩሉ ክፍያው ለአገልግሎቱ አስፈላጊ የመሠረተ ልማት ማስኬጃ እንደሆነ በመግለጽ ውሳኔውን የተከላከለ ቢሆንም፣ በ2016/17 የበጀት ዓመት ወጪያቸው  ወደ 81.3% ከፍ ላለው ባንኮች ይህ አዲስ አሠራር ተጨማሪ የፋይናንስ ጫና ፈጥሮባቸዋል።

@Yenetube Fikerassefa
10 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.