የማታለል ወንጀል የፈጸሙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ/ም ከቀኑ 7፡00 ሠዓት ገደማ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ልዩ ቦታው ደሳለኝ ሆቴል አካባቢ ነው፡፡
ተከሳሾች ካሳሁን አለሙ ፣ እንዳለው ቸኮል እና ትሚዝ ቢያሳዝነው የተባሉ ሲሆኑ በተጠቀሰው ቦታ ላይ አንድ የኩባ ዜግነት ያላቸውን የግል ተበዳይ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አ/አ 51708 ኮሮላ ተሽከርካሪ በመያዝና የሠሌዳ ቁጥሩ እንዳይታይ በመፋቅ በግል ተበዳይ ላይ ምራቃቸውን በመትፋትና ይቅርታ በመጠየቅ የጠረጉ በመምሰል ከኪሳቸው ውስጥ የዋጋ ግምቱ 97ሺህ ብር የሚያወጣ አይፎን 13 ስልክ በመስረቅ ተሰውረዋል፡፡
የግል ተበዳይም የተፈፀመባቸውን ወንጀል የዜጎች ተሳትፎ መተግባሪያ Citizen Engagemnet Application EFPApp በመጠቀም ለፖሊስ ሪፖርት አድርገዋል፡፡
በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የአደይ አበባ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ የምርመራና የክትትል ቡድን ወንጀሉ የተፈፀመበት ቦታ በመሄድ ተገቢውን ማስረጃ በማሰባሰብ ባከናወኑት የምርመራ ተግባር ሦስቱንም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ሊያውላቸው መቻሉን የቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የወንጀል ምርመራ ም/ዋና መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ኤፍሬም አለሙ ገልጸዋል።
ተጠርጣሪዎች በተያዙበት ወቅትም ለወንጀል መፈፀሚያነት የሚጠቀሙባቸው የተለያዩ ቁሳቁሶች ጋር በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑንም ኃላፊው አስታውቀዋል፡፡
ህብረተሰቡ የሚፈፀሙ የወንጀል ድርጊቶችን ከመደበኛው የፖሊስ የመረጃ ስልኮች በተጨማሪ ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረጉ ጥቆማዎች ሊበረታቱ ይገባቸዋል ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ጥቆማ የመስጠት ባህሉንም ማጠናከር እንዳለበት መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

10 days ago