Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኡስማን ሳላህ የተመራው የኤርትራ ልዑካን ቡድን በ81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል። የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል ባወጡት መረጃ መሰረት ሚኒስትር ኡስማን ሳላህ ከተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር በወቅታዊ ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸው ወቅት ሚኒስትር ኡስማን፣ የኢትዮጵያ ገዥው ብልጽግና ፓርቲ በጎረቤት ሀገራት ላይ የተመድን ቻርተር እና የዓለም አቀፍ ህግጋት መሰረታዊ መርሆችን በግልጽ የጣሰ የትንኮሳ ድርጊት እየፈጸመ ነው ሲሉ ከሰዋል።

በተጨማሪም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በዚሁ መድረክ ላይ በሱዳን እና በቀይ ባህር ጉዳዮች ላይ የሀገራቸውን አቋም አብራርተዋል። ኤርትራ የተባበረች፣ ሉዓላዊነቷ የተከበረ እና የተረጋጋች ሱዳንን እንደምትደግፍ ገልጸው፤ በሱዳናውያን ባለቤትነት የሚመራ እና በቀጠናዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት የሚደገፍ አካታች የፖለቲካ ሂደት እንዲኖር ጠይቀዋል። የቀይ ባህር እና የባብ-ኤል ማንደብ ደህንነትን በተመለከተም፣ የባህር ዳርቻ ሀገራትን ሉዓላዊነት እና ህጋዊ ፍላጎት ባከበረ መልኩ ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር ላይ ጉዞ እና ዓለም አቀፍ ትብብርን ኤርትራ እንደምትደግፍ አረጋግጠዋል።

ሚኒስትሩ የሀገራት ሉዓላዊ እኩልነት፣ የግዛት አንድነት፣ የፖለቲካ ነጻነት፣ በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት እና ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት የሚሉት የተመድ መርሆች አሁንም ወሳኝ መሆናቸውን አስምረውበታል። በሌላ ዜና፣ ኤርትራ የ81ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆና የተመረጠች ሲሆን፣ አምባሳደር ሶፊያ ተስፋማሪያም ኤርትራን ወክለው በጉባኤው መክፈቻ ዕለት የምሽቱን የምክክር መድረክ በምክትል ፕሬዝዳንትነት መምራታቸው ታውቋል።

12 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.