የ8 አመት ልጅ በመሸሸግ 3 ሚሊዮን ብር የጠየቀች የቤት ሰራተኛ በቁጥጥር ስር ዋለች‼️
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ/ም ከምሽቱ 4፡00 ሠዓት በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ካርል አደባባይ ከሚገኝ አንድ መኖሪያ ቤት ነው፡፡
ሰናይት አየለ የተባለች ግለሰብ በግል ተበዳይ መኖሪያ ቤት በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ መስራት ከጀመረች 8 ወራት ያህል አስቆጥራለች፡፡
ተጠርጣሪዋ በተገለፀው ቀንና ሠዓት ዘዊ ጠንክር የተባለች የ8 አመት ህፃን ልጅ የግል ተበዳይ ከሚኖሩበት አፓርታማ ሁለተኛው ፎቅ ላይ ለኪራይ ተብሎ በተዘጋጀ ክፍል ውስጥ ህፃኗን ሸሽጋ እንድትቀመጥ አድርጋለች፡፡
ተከሳሽ ህፃኗን ከሸሸገች በኋላም ለአባቷ በመደወልና ልጃቸው መታገቷን በመግለፅ ለማስለቀቅ 3 ሚሊየን ብር እንዲከፍሉ ጠይቃለች፡፡
የግል ተበዳይም የወንጀል ድርጊቱ ከተፈፀመ በኋላ ለፖሊስ በሰጡት መረጃ ፖሊስ ጉዳዩን ሲከታተል ቆይቶ 24 ሠዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ተከሳሽን በቁጥጥር ስር ሊያውልም ችሏል፡፡
ህፃኗ በመልካም ጤንነት ላይ መሆኗን የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የቤት ሰራተኞች ከመቀጠራቸው በፊት ተገቢው ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበትም መልዕክቱን አስተላልፏል።
አዲስ ፖሊስ
Seledadotio

12 days ago