ኔታንያሁ በተመድ፦ «እኛ እናሸንፋለን፤ ከዚህ ውጪ ሌላ አማራጭ የለንም»
#ethiopia | የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢንያም ኔታንያሁ፣ እየጨመረ በመጣው ዓለም አቀፍ ጫና ውስጥ ሆነው የእስራኤልን አቋም ለዓለም ለማስረዳት በተባበሩት መንግሥታት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር አደረጉ።
ኔታንያሁ ወደ መድረኩ ሲወጡ የበርካታ ሀገራት ልዑካን አዳራሹን ለቀው የወጡ ሲሆን፣ ሌሎች ደግሞ በጭብጨባ ተቀብለዋቸዋል። ከእስራኤል ልዑካን ቡድንም «አም ይስራኤል ኻይ» የሚል፣ «የእስራኤል ሕዝብ በሕይወት ይኖራል» የሚል መፈክር ተሰምቷል።
ኔታንያሁ ንግግራቸውን ሲጀምሩም አዳራሹን ለቀው ለወጡት ልዑካን «ሌሎች የሞራል ፈሪዎች ካሉ እባካችሁ አሁኑኑ ውጡ» ሲሉ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከ14 ዓመታት በፊት በተመድ የኢራንን የኑክሌር ፕሮግራም ለማስጠንቀቅ የቦምብ ምስል በማሳየት ቀይ መስመር ማስመራታቸውን አስታውሰዋል።
«የኢራን አምባገነን መንግሥት አቶሚክ ቦምብ እንዳታደራጅ ለመከላከል ቃል ገብቼ ነበር፤ ያደረግኩትም በትክክል እሱን ነው» ብለዋል።
የኢራንን የኑክሌር ፕሮግራም ማፍረስ «በጣም ከባድ» ቢሆንም፣ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ካሳለፏቸው ውሳኔዎች ሁሉ ቀላሉ ውሳኔ እንደነበር ገልጸዋል።
ኔታንያሁ እስራኤል ራሷን በመከላከል አዳራሹን ለቀው የወጡትን ሀገራት ጭምር እንደታደገች ገልጸው፣ የእነዚህ ሀገራት መሪዎች በግል እንደሚያመሰግኗቸው ተናግረዋል። ይህንንም «ዓለም አቀፍ ግብዝነት» ሲሉ ገልጸውታል።
ለሶሪያው ፕሬዝዳንት አህመድ አል-ሻራዕ ምላሽ ሲሰጡም፣ አይሁዶች በጎላን ኮረብታዎች ላይ ከሙሴ ዘመን ጀምሮ ይኖሩ እንደነበር ጠቅሰው፣ ይህንንም በመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ እንደሚቻል ተናግረዋል።
እስራኤል ከአጠቃላይ የአረብ ምድር 0.3 በመቶ ብቻ የምትሸፍን ትንሽ ሀገር መሆኗን የጠቀሱት ኔታንያሁ፣ እስራኤልን «ቅኝ ገዥ» በማለት የሚቀርብባትን ክስ አጣጥለዋል።
«ቅኝ ገዥነትን ፈጥረው ዓለምን በሙሉ የገዙት የእንግሊዝ እና የፈረንሳይ ሰዎች እኛን ይከሰናሉ» ብለዋል።
በ1967 ዓ.ም. በተካሄደው ጦርነት ወቅት ወንድማቸውን ዮኒ ኔታንያሁን ለመጎብኘት ወደ ጦር ግንባር በሄዱበት ወቅት ወንድማቸው «እኛ እናሸንፋለን፤ ከዚህ ውጪ ሌላ አማራጭ የለንም» እንዳላቸው አስታውሰዋል።
ይህ አባባል ዛሬም ለእስራኤል የሚሰራ መሆኑን የገለጹት ኔታንያሁ፣ ኦክቶበር 7 ቀን 2023 የእስራኤል ታሪክ «ጨለማው ቀን» እንደነበር ገልጸዋል።
«ጠላቶቻችን እስራኤል ትወድቃለች ብለው አስበው ነበር፤ አልወደቅንም። ይልቁንም ተነስተን እንደ አንበሳ ተዋጋን» ብለዋል።
እስራኤል ከአሜሪካ ጋር በመተባበር በበርካታ ግንባሮች መዋጋቷን የጠቀሱት ኔታንያሁ፣ በኢራን ላይ የተወሰዱ የጦር እርምጃዎችን፣ እንዲሁም ሐማስና ሂዝቦላህ ላይ የተወሰዱ ወታደራዊ እርምጃዎችን ጠቅሰዋል።
በንግግራቸው ወቅት ፔጀር ከኪሳቸው በማውጣትም የሂዝቦላህ አባላት በ2024 በተካሄደው የፔጀር ፍንዳታ ጥቃት የተጎዱበትን ክስተት አስታውሰዋል።
በይሁዳና ሰማሪያ የሚፈጸሙ የሽብር ጥቃቶች በዓለም አቀፍ ሚዲያ በቂ ሽፋን እንደማያገኙ የተናገሩት ኔታንያሁ፣ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በአንዳንድ የሰፋሪዎች ጥቃት ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሲሰጡ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ በሺዎች የሚቆጠሩ ጥቃቶችን ችላ እንደሚሉ ከሰዋል።
«እኛ የሕግ ሀገር ነን፤ ሺን ቤትንም በእነሱ ላይ አሰማርተናል» ያሉት ኔታንያሁ፣ ይህንን የሚዲያ አቀራረብ «ትልቅ ማዛባት» ብለው ንግግራቸውን ደምድመዋል።

12 days ago