Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣናትን ያካተተ የልኡካን ቡድን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ኒውዮርክ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ የአሜሪካ የግምጃ ቤት ሀላፊ የሆኑት ስኮት ቤሴንት የልኡካን ቡድኑን በተመለከተ አስቸጋሪ ጥያቄ አንስተዋል፡፡ ይህም ‹‹እንዴት ወደአገራቸው ይመለሳሉ?›› የሚል ነው፡፡ ቤሴንት ለፎክስ ኒውስ በሰጡት መግለጫ ሲናገሩ ‹‹በተመድ ስብሰባ እየተሳተፉ ያሉት የኢራን ተወካዮች እንዴት እንደሚመለሱ እርግጠኛ አይደለሁም›› ካሉ በኋላ አሜሪካ በኢራን አየር መንገዶችና አለም አቀፍ የአየር ግንኙነት ላይ የጣለችውን ማእቀብ አንስተዋል፡፡

ፕሬዝደንት መሱድ ፔዜኪሺያንና የልኡካን ቡድናቸው ኒውዮርክ የገቡት ማክሰኞ እለት ሲሆን ከ5 ቀን ቆይታ በኋላ ቅዳሜ ወደቴሄራን ለመመለስ አቅደዋል፡፡ ይሁንና ቅዳሜ አዲሱ የአሜሪካ የአቪየሽን ማእቀብ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ 3ተኛ ቀን ይሆነዋል፡፡ የዋሽንግተን መንግስት ‹‹ኦፐሬሽን ኢኮኖሚክ አውትካስት›› በሚል የሰየመውን ማእቀብ ያወጣው ሴፕቴምበር 8 ቀን የነበረ ሲሆን በዚህም በሁሉም የኢራን አየር መንገዶች ላይ እገዳን ጥሏል፡፡ ይህ እርምጃ በ27 አየር መንገዶች ላይ ያነጣጠረ ከመሆኑም በላይ የኢራንን አቪየሽን በርፍ በመደገፍ ተሳትፎ ያላቸው ሌሎች ድርጅቶችም የማእቀቡ ሰለባ እንደሚሆኑ ማስጠንቀቂያ የሰጠ ነው፡፡ ማእቀቡን ተግባራዊ ከማድረጉ በፊት የሰጠው ቀነ ገደብ ሴፕቴምበር 23 ቀን በመጠናቀቁ የተነሳ ትላንት ከሮብ እለት አንስቶ ተፈፃሚ መሆን መጀመሩንም አስታውቋል፡፡

በማእቀቡ ለኢራን አየር መንገዶች ነዳጅ የሚሞሉ፣ ማረፊያ የሚፈቅዱና ትኬት የሚሸጡ ጭምር ክልከላ የተጣለባቸው ሲሆን ቤሴንት ቀደም ብለው በሰጡት መግለጫ ‹‹ከሮብ ጀምሮ የኢራን አየር መንገዶች ይዘጋሉ›› ብለው ነበር፡፡ በእርግጥ እንዳሉትም ከትላንት አንስቶ ከ80 እስከ 90 ፐርሰንት የሚሆነው የኢራን አየር መንገዶች እንቅስቃሴ ቆሟል፡፡ ወደአዘርባጃን፣ ባግዳድ፣ ሙስካትና ሌሎችም ከተሞች የሚደረጉ አለም አቀፍ በረራዎች ተሰርዘዋል፡፡ የቱርክ አየር መንገድም እስከ ማርች 2027 ድረስ ወደኢራን የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡን አስታውቋል፡፡ ይሁንና አንዳንድ የኢራን አለም አቀፍ በረራዎች እንደቀጠሉም ይገኛሉ፡፡

ለምሳሌ ወደቻይና የሚደረጉ በረራዎች ዛሬም ቀጥለዋል፡፡ የኢራኑ ፕሬዝደንትና ልኡካን ቡድናቸው ወደኒውዮርክ የተጓዙት ይህ ማእቀብ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ቢሆንም በተለይ ፕሬዝደንቱ የተጓዙት በመደበኛ የኢራን የተሳፋሪዎች በረራ አይደለም፡፡ ፕሬዝደንቱ የተሳፈሩት በአሺያኔህ ባለቤትነት በሚተዳደር ኤይር ባስ 340 አውሮፕላን ሲሆን ይህ ድርጅት እንብዛም የማይታወቅ የኢራን አየር መንገድ ነው፡፡ አሺያኔህ በመደበኛነት የመንገደኞች አገልግሎት የማይሰጥ ወይንም ትኬት የማይሸጥ በመሆኑ በአሜሪካና በአውሮፓ ህብረት ማእቀብ ውስጥ እስካሁን አልተካተተም፡፡ የፍላይት ራዳር መረጃ እንደሚያሳየው አውሮፕላኑ ወደኒውዮርክ ከመድረሱ በፊት በአልጀርስ ቆሞ ነበር፡፡

ፕሬዝደንት ፔዜሽኪያን ወደቴሄራን ለመመለስ ያቀዱት በዚህ አውሮፕላን ይሁን አይሁን እስካሁን የተባለ ነገር የለም፡፡ ይህ አውሮፕላን ነዳጅ ለመሙላትና ሌሎችንም አገልግሎቶች ለማግኘት ችግር ይገጥመው ይሆን የሚለውም ግልፅ አይደለም፡፡ የኢራን ልኡካን ቡድን እንዴት ወደአገሩ ይለመለሳል? የሚለው ጥያቄ መልስ የሚያገኘውም ቅዳሜ ብቻ ነው፡፡ ለጊዜው የሚታወቀው ፔዜሽኪያን በኒውዮርክ ማጠናቀቅ ያለባቸውን ስብሰባዎች እየተካፈሉ መሆኑ ነው፡፡

13 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.