Logo
ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal
የአሜሪካ ማዕቀብን ተከትሎ ኢራን ወደ ኢራቅ እና ኦማን የምታደርጋቸውን በረራዎች ሰረዘች፡፡

በአሜሪካ ማዕቀቦች ጫና ምክኒያት፣ ኢራን ቀጠናዊ ዓለም አቀፍ በረራዎችን ለመሰረዝ ተገዳለች።

የሀገሪቱን የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ጠቅሰው የኢራን መገናኛ ብዙሀኖች እንደዘገቡት፣ ከረቡዕ ጧት ጀምሮ ኢራቅ እና ኦማን ከኢራን የሚነሱ በረራዎችን አያስተናግዱም ብለዋል።

የአሜሪካ የግምጃ ቤት ሚኒስትር ስኮት ቤሴንት ሰኞ ዕለት በሰጡት ቃለ ምልልስ በኢራን የአቪዬሽን ዘርፍ ላይ ተጨማሪ ጫና እንደሚደረግ ነው ያስታወቁት።የኢራን አየር መንገድ ኩባንያዎችን ነዳጅ የሚያቀርቡ፣ የማረፊያ አገልግሎት የሚሰጡ ወይም በእነሱ ስም ቲኬት የሚሸጡ ሀገራት ከአሜሪካ ዶላር ስርዓት እንደሚገለሉ አስጠንቅቀዋል።

የኢራን አቪዬሽን ባለስልጣን ቃል አቀባይ ማጂድ አኻቫን በበኩላቸው፣ ኢራን ወደ ኢራቅ የምታደርጋቸውን በረራዎች በሌላ አየር ማረፊያ በኩል ለማስቀጠል እየሰራች መሆኗን መናገራቸውን ኢስና የዜና ወኪል ዘግቧል።

በተመሳሳይ የኢራን አየር መንገድ ኩባንያዎች ወደ ጎረቤት አዘርባጃን የሚያደርጓቸው በረራዎችም በአፋጣኝ መታገዳቸውን የአዘርባጃን አየር መንገድን ጠቅሶ ሻርግ የተባለው ጋዜጣ ዘግቧል።

በሚኪያስ ጸሐዬ
#ዳጉ_ጆርናል
15 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.