Logo
4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ™
አምስተኛው የአውሮፓ ሀገራት ሊግ (ኔሽንስ ሊግ) ዛሬ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራል
*******

እ.አ.አ በ2018 ጅማሮውን ያደረገው የአውሮፓ ሀገራት ሊግ ዛሬ በተለያዩ ከተሞች በሚደረጉ ጨዋታዎች ጅማሮውን ያደርጋል።

በምድብ አራት ምሽት 3፡45 የሁለት ጊዜ ሻምፒዮኗ ፖርቹጋል ከዌልስ የሚያደርጉት ጨዋታ ከዕለቱ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች አንዱ ነው። በእግር ኳስ ህይወቱ ያስቆጠራቸውን ግቦች 1ሺህ ለማድረስ እየተንደረደረ የሚገኘው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ አሁንም የትኩረት ማዕከል እንደሆነ ቀጥሏል።

በአዲሱ አሰልጣኝ ሆርጌ ጄሱስ የሚመራው የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን፣ በ23ኛው ዓለም ዋንጫ በ16ቱ ጥሎ ማለፍ የተቋረጠውን መንገዱን ለማቃናት የኔሽንስ ሊግ ጨዋታውን ያደርጋል።

ለ23ኛው ዓለም ዋንጫ ያላለፈበትን ጨምሮ ከጋሬዝ ቤል ስንብት በኋላ የውጤት ማሽቆልቆል የተስተዋለበት የዌልስ ብሔራዊ ቡድን በቀድሞ የሊቨርፑል እና ማንቸስተር ሲቲ ኮከብ ክሬግ ቤላሚ አሰልጣኝነት እየተመራ ጨዋታውን ያደርጋል።

ሁለቱ ሀገራት በታሪካቸው የተገናኙት አራት ጊዜ ሲሆን ሦስቱ በፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን አሸናፊነት ሲጠናቀቅ፣ አንዱ ደግሞ በአቻ ውጤት ነው ፍፃሜውን ያገኘው።

ባለፉት ሁለት ዓመታት በዕረፍት አሳልፈው የጀርመን ብሔራዊ ቡድንን የተረከቡት ውጤታማው አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ወደ አምስተርዳም አቅንተው የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድንን በመግጠም ጉዟቸውን ይጀምራሉ።

በ23ኛው ዓለም ዋንጫ በፓራጓይ ተረቶ ከ32ቱ ሀገራት ጥሎ ማለፍ የተሰናበተው የጀርመን ብሔራዊ ቡድን፣ በቀደመው ውድድር 4ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀበት የኔሽንስ ሊግ ትልቁ ውጤቱ ነው።

በቀድሞ የባርሴሎና ኮከብ ዣቪ ኸርናንዴዝ የሚመራው የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድን በአንፃሩ በ2018 ውድድር እስከ ፍፃሜ የመጓዝ ታሪክ አለው።

በዮሃን ክራይፍ ስታዲየም የሚደረገው የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ ምሽት 3፡45 ይጀምራል።

ሰርቢያ ከ ግሪክ፣ ኖርዌይ ከ ዴንማርክ፣ ኦስትሪያ ከ እስራኤል እንዲሁም ኮሶቮ ከ አየርላንድ ሌሎቹ የዛሬ የኔሽንስ ሊግ መርሐ ግብሮች ናቸው።( EBC Sport )

@Bisrat_sport_433et @Bisrat_sport_433et
13 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.