Logo
FBC
የዛሬ ምሽት ዜና መፅሔት ጉዳዮች

👉የአደባባይ በዓላት በተለየ ሁኔታ የመስከረም ወር መድመቂያ ናቸው፡፡ እነዚህ በዓላት ለቱሪዝም ዘርፉ ያላቸው አስተዋፅኦ ቀላል አይደለም፡፡ የቱሪዝም ሚኒስትሯ በቀጣይ የሚከበሩ የአደባባይ በዓላትን አስመልክቶ መግጫ ሰጥተዋል፡፡ በመፅሔቱ ይዘነዋል፡፡

👉የመንግሥትና የህዝብ የጠበቀ ትብብርና የባለቤትነት ስሜት ሀገርን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር እና የልማት ስራዎችን ግብ ለማድረስ ቁልፍ ሚና አለው። አዲስ የሚመሰረተው መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ይጠበቅበታል? ይተነተናል፡፡

👉ኢትዮጵያ ልዩነቶቿን በምክክርና በመደማመጥ በመፍታት ወደ ዴሞክራሲያዊ መግባባት እየተሸጋገረች መሆኗ ማሳያዎቿ ብዙ ናቸው፡፡

👉በቀይ ባሕር ጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ውስጥ፣ ኢትዮጵያ የቀጣናውን ሰላምና የኢኮኖሚ ትስስር እውን ለማድረግ ያላትን ወሳኝ ሚና በተግባር የምታሳይበት ወርቃማ ጊዜ መጥቷል፡፡ ጉዳዩ የኢትዮያን መሻት ለማስከበር እና እውነቷን ለማስመስከር ድርሻው ምን ድረስ ነው? በምሁራን ይተነተናል፡፡

👉ኢትዮጵያ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ከአስተያየት ሰጪነት ወደ አጀንዳ ቀራፂነት መሸጋገሯ ብሔራዊ ጥቅሞቿንና የፋይናንስ አማራጮቿን ለማስፋት የከፈተችው ወርቃማ በር በብሪክስ እና በባህር በር ዲፕሎማሲ ማዕቀፍ እንዴት ይታያል?

👉ከውጭ፡ አሜሪካ ኒኮላስ ማዱሮን ከስልጣን ካወረደች በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕና የቬንዙዌላ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ገጽ ለገጽ ተወያዩ፡፡ የተወያዩባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ምንድን ናቸው? በትንታኔ ይደርሳችኋል፡፡

በስፖርት ሰዓታችን - አዳዲስ እለታዊ መረጃዎችን እናደርሳችኋለን፡፡

የዜና ክፍል ጋዜጠኞች እነዚህን ጨምሮ ሌሎች ዘገባዎችን አካተው በፋና የምሽቱ ዜና መፅሔት ሊያስደምጧችሁ ዝግጁ ናቸው ።

ማርታ ጌታቸው ትጠብቃችኋለች።

በኤፍ ኤም 98 .1 እና በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ ኤፍ ኤሞቻችን እንዲሁም በwww.fanamc.com በመላው ሀገሪቱና በዓለም ዙሪያ ስርጭታችንን መከታተል ትችላላችሁ።

ከምሽቱ 1 ሰዓት ይጠብቁን

14 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.