Logo
YenetaTube
መስከረም 25 የአዲሱ መንግሥት ምስረታ ይደረጋል ተብሏል

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባወጣዉ መረጃ መሠረት የ7ተኛ ጠቅላላ ምርጫ ዉጤት መሠረት አዲስ የመንግስት ምስረታ እና የምክር ቤቱ የመክፈቻ ስነስርዓት የሚደረግ መሆኑን ገልጿል።

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በመስከረም ወር የመጨረሻ ሰኞ የምክር ቤቱ የስራ ዘመን እንደሚጀመር አስታዉሰዋል።

በሌላ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 56 በምክር ቤቱ አብላጫ ድምፅ ያገኘ የፓለቲካ ድርጅት የፌደራሉ መንግስት የአስፈጻሚ አካል የሚያደራጅ መሆኑን ደንግጓል፡፡

በዚህ መሠረት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም የመንግስት ምስረታ ይካሄዳል ማለታቸዉን የምክር ቤቱ ማህበራዊ ትስስር ገፅ መረጃ ጠቁሟል።

14 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.