Logo
EBC
ተመድ ኢትዮጵያ ለምታስተናግደው ኮፕ 32 ጉባኤ ሙሉ ድጋፍ ያደርጋል - አንቶኒዮ ጉተሬዝ
*****************

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በስፋት ተወያይተዋል።

ሁለቱ ወገኖች በኒውዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ባደረጉት በዚህ ውይይት፤ በዋናነት በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የሰላምና የደህንነት ሁኔታ እንዲሁም ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

በውይይቱ ወቅት የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ኢትዮጵያ በዘላቂ ልማት ዘርፍ እያመዘገበች ያለችውን አበረታች ስኬት ያደነቁ ሲሆን፤ ሀገሪቱ በቅርቡ ለምታስተናግደው ታሪካዊው 32ኛው የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤ ድርጅታቸው አስፈላጊውን ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ ከተመድ ዋና ጸሐፊ ጋር ያደረጉት ውይይት በቀጣናው ዘላቂ ሰላምን፣ ደህንነትንና ልማትን ለማረጋገጥ ያለመና የጋራ ትብብርን ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑን ጠቁመዋል።

14 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.