Logo
FastMereja
በሕይወት እያለ የራሱን የሐዘን ባነር ያዘጋጀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ
#fastmereja I በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቤንች ሸኮ ዞን ሰሜን ቤንች ወረዳ ኦካ ቀበሌ፣ በሕይወት እያለ የራሱን ፎቶ በመጠቀም "ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል" የሚል የሐሰት የሐዘን መግለጫ ባነር አዘጋጅቷል የተባለ ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሄደበት ይገኛል።

​የሰሜን ቤንች ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ዘለቀ ኮሽካ እንደገለጹት፣ ድርጊቱ በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥንና አለመረጋጋትን የፈጠረ ነው። አዛዡ አክለውም ያልተከሰተን የሞት ክስተት እንደተከሰተ አስመስሎ ማቅረብ አሳዛኝ የስነ-ምግባር ግድፈት መሆኑን ጠቁመዋል።

​ምክትል ኢንስፔክተሩ ህብረተሰቡ ማናቸውንም መረጃዎች ሳያጣራ እንዳያምንና ከተጨባጭ እውነት የራቁ የሐሰት ወሬዎችን በጥንቃቄ እንዲመለከት አሳስበዋል። በማህበረሰቡ ሰላምና ደህንነት ላይ የሚቀልዱና የህዝብን ስነ-ልቦና የሚነኩ ድርጊቶችን በሚፈጽሙ አካላት ላይ ፖሊስ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን እንደሚቀጥልበትም አስታውቀዋል።

​ጉዳዩን የሰሜን ቤንች ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን የዘገበው ሲሆን፣ በግለሰቡ ላይ የሚደረገው የፖሊስ ምርመራ ተጠናቆ ህጋዊ እርምጃ እስኪወሰድ ድረስ ክትትሉ ይቀጥላል።

15 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.