የማዕድን ዘርፍ፡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አዲሱ ምሰሶ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የመደመር መንግሥት ሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን ካስቀመጣቸው አምስት ዋና ዋና የሀገር ኢኮኖሚ እድገት ምሰሶዎች መካከል የማዕድን ዘርፍ አንዱና ወሳኙ የትኩረት አቅጣጫ ነው።
ኢትዮጵያ በመሬቷ ጉያ እጅግ በርካታ የከበሩ ማዕድናት ሀብት የታደለች ቢሆንም፣ ቀደም ባሉት ዓመታት ዘርፉ ለሀገር ኢኮኖሚ ያበረከተው አስተዋጽኦ ከአቅሙ አንጻር ሲታይ አነስተኛ ነበር።
የመደመር መንግሥት ይህንን ክፍተት ለመሸፈን በዘርፉ መዋቅራዊ ማሻሻያ በማድረግ፣ የውጭና የሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንትን በመሳብ እና የሕገ-ወጥ ንግድን በመግታት የላቀ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል።
ውስብስብ የነበሩ የአሠራር ሥርዓቶችን በማቃለል፣ ግልጽነትን በመፍጠር እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የሚያስችሉ አዳዲስ የሕግ ማዕቀፎች እና የፈቃድ አሰጣጥ ደንቦች በማዘጋጀት ሥራ ላይ ውለዋል።
በሺዎች የሚቆጠሩ በባህላዊ መንገድ ይሠሩ የነበሩ ማዕድን አውጪዎች በማኅበር እንዲደራጁ፣ የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ ከሕገ-ወጥ ንግድ ወደ ሕጋዊ ሥነ-ምህዳር እንዲገቡ ተደርጓል።
ጥሬ ማዕድናትን በቀጥታ ከመላክ ይልቅ በሀገር ውስጥ እሴት እንዲጨመርባቸው የሚያስችሉ የኢንዱስትሪ ማዕከላትና የማጣሪያ ፋብሪካዎች፣ ማለትም የወርቅና የከበሩ ድንጋዮች ማጣሪያዎች እንዲገነቡ በማበረታታት በርካቶች ወደ ሥራ እንዲገቡ ተደርጓል።
እንደ ወርቅ፣ ታንታለም፣ ሊቲየም፣ እብነ-በረድ ፣ ፖታሽ እና የድንጋይ ከሰል የመሳሰሉ ማዕድናት በሰፊው እንዲመረቱ በማድረግ ወደ ውጭ በመላክም ሆነ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ከማስገኘትና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ከመተካት አንጻር ከፍተኛ ሥራ በመሠራት ላይ ይገኛል።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በኩል የሚደረገውን የወርቅ ግዥ ማበረታታትን ጨምሮ በተወሰዱ ርምጃዎች፣ በሕገ-ወጥ መንገድ ይወጣ የነበረውን ወርቅ ወደ ሕጋዊ መስመር በማስገባት ከወርቅ ወጪ ንግድ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ተችሏል።
በዚህም እንደ ማዕድን ሚኒስቴር መረጃ፥ በ2018 ዓ.ም. የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራት ብቻ ከማዕድን ወጪ ንግድ ከ4 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል።
ይህም ከሦስት ዓመታት በፊት የሀገሪቱ አጠቃላይ ዓመታዊ የኤክስፖርት ገቢ የነበረውን ያህል መሆኑ፣ ዘርፉ በተሰጠው ትኩረት በጥቂት ዓመታት ያመጣውን ትልቅ ስኬት ያሳያል።
በአጠቃላይ በ2018 በጀት ዓመት ከማዕድን ምርት ከ5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኝቷል።
ለግንባታ ግብዓት ኢንዱስትሪዎች የሚያገለግለውን የድንጋይ ከሰል ምርትን በሀገር ውስጥ ለማምረት በተደረገው ጥረት፣ ለሲሚንቶ እና ለሌሎች ኢንዱስትሪዎች የሚሆን የድንጋይ ከሰል በማምረት ከውጭ ሀገር የሚገባውን በመተካት በቢሊየን ዶላር የሚቆጠር ወጪን አስቀርቷል።
ይህ ዘርፍ ለብዙ ሺህ ወጣቶች፣ በተለይም በማዕድን ሀብት በበለጸጉ አካባቢዎች፣ ከፍተኛ የሥራ ዕድል መፍጠር ችሏል።
በአጠቃላይ በመደመር መንግሥት የማዕድን ዘርፉ የውጭ ምንዛሪ ለማስገኘት እና የገቢ ምርቶችን ለመተካት እንደ ዋና አምድ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል።
በቀጣይ የተጀመሩትን ሥራዎች ማለትም የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎችን በማስፋፋት፣ ሕገ-ወጥ ንግድን በመቆጣጠር እንዲሁም የውጭ ኢንቨስትመንትን አጠናክሮ በመሳብ ዘርፉ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እመርታ የሚጫወተውን ሚና ይበልጥ ማጠናከር ይገባል።
በመልካም ፈቃዱ

15 days ago