Logo
Getu Temesgen
🔴ከመቶ አለቃ ወደ ብርጋዴር ጄኔራል
የፕሪሚየር ሊጉ የስልጣን ሽግግር
#ethiopia | የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ 8ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ሲያደርግ የመጨረሻው የስልጣን ሹመት ሽግግርን ከመቶ አለቃ ወደ ብርጋዴር ጄኔራል አድርጎል።

አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ በተከናወነበት የዛሬ ምርጫ
ለቀጣይ 3 አመታት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ ዳይሬክተሮች ቦርድና 7 አባላት ምርጫ ተከናውኗል።

በቦርድ አባላት በተደረገ የስራ ኃላፊነት ክፍፍል
የመቻል ስፖርት ክለብ ፕሬዝዳንት የሆኑት ብ/ጄ ኑሩ ሙዘይን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ሲሆኑ አቶ መንግስቱ ታደሰ ከኢትዮጵያ ቡና የዳይሬክተሮች ቦርድ ም/ሰብሳቢ ሆነው ተመርጠዋል።

👉ሰባቱ የሊግ ካምፓኒው አመራሮች
🔴 ብ/ጄ ኑሩ ሙዘይን(መቻል)
🔴 አቶ መንግስቱ ታደሰ(ኢትዮጵያ ቡና)
🔴አቶ ልዑል ፍቃዱ(ባህር ዳር ከተማ)
🔴 አቶ ተስፉ ተክሌ(ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
🔴 አቶ መንግስቱ አባይነህ(ኢትዮ ኤሌክትሪክ)
🔴አቶ ታገል ጌታቸው(ሀላባ ከተማ)
🔴 ወ/ሮ ከነዓን በለጠ(ሲዳማ ቡና) በመሆን ተመርጠዋል።

✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

17 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.