የኢኮኖሚ ዋልታነቱን እያረጋገጠ የሚገኘው የቡና ምርት
********************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በዓለም ላይ የኮፊ አረቢካ መገኛ ብቻ ሳይሆን፣ ትልቋ አምራች ሀገር የሚል ስም መያዝ እንዳለባትና የኢኮኖሚ ዋልታ ዘፈን ሳይሆን ተግባር መሆን እንደሚገባ ማስገንዘባቸው ይታወሳል።
በመሆኑም “የኢኮኖሚ ዋልታ ቡና ቡና” እየተባለ የተዜመለት የኢትዮጵያ ቡና፣ ዛሬ ላይ በተጨባጭ የውጭ ምንዛሪ ግኝት እና በሰፊ የምርት ማሻሻያ ሥራዎች ሀገራዊ ኢኮኖሚውን እየደገፈ ይገኛል።
የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ በተከናወኑ ሥራዎች፣ ዓመታዊ የቡና ምርት መጠን ከነበረበት በየዓመቱ ከፍተኛ ዕድገት እያሳየ ይገኛል። ዘመናዊ የቡና መስኖ ልማት እና በማሽን የታገዘ የቡና ለቀማ የአርሶ አደሮችን ሕይወት በማቅለል የቡና ምርት ጥራትን ከፍ አድርጓል።
ኢትዮጵያ በ2018 በጀት ዓመት ከቡና ወጪ ንግድ ከ3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም ሀገራችን ባለፉት 17 ዓመታት በአጠቃላይ ካገኘችው 3 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር የገቢ መጠን ጋር የሚቀራረብ መሆኑን ያሳያል።
የቡና ጥራትን ማስጠበቅና ምርታማነትን ማሳደግ በዓለም አቀፍ ገበያ ይበልጥ ተወዳዳሪ ለመሆን እንደሚረዳ የቡና አምራቾች እና ላኪዎች የሚናገሩ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የቡና ምርት ልማትና ጥራት በየጊዜው ዕድገት በማሳየት በተለይም የልዩ ጣዕም ቡና በገበያ ላይ ተፈላጊነቱ በእጅጉ ጨምሯል።
የቡናው ዘርፍ ከባህላዊ አሠራር ወጥቶ በቴክኖሎጂ፣ በጥራት እና በመስኖ ልማት እንዲዘምን ማድረግ የነገዋን የበለጸገች ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ ቁልፍ ሚና አለው።
የላኪዎችን፣ የአርሶ አደሮችን እና የመንግሥትን የተቀናጀ ጥረት አጠናክሮ መቀጠል፣ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ገበያ የኮፊ አረቢካ መገኛ ብቻ ሳትሆን ትልቋ እና ተወዳዳሪዋ የቡና አምራች ሀገር ማድረጉ የማይቀር እውነት ነው።
በሐይማኖት ከበደ
#ebc #greenlegacy #ethiopiancoffee #agritech #sustainableagriculture

19 days ago