ባህልን የልማትና የትውልድ ግንባታ መሳሪያ ያደረገው የመደመር መንግሥት
አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የመደመር መንግሥት በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ቋንቋዎች፣ እምነቶች፣ ታሪኮች እና ባህሎችን በማቀራረብና በመደመር ለጋራ ብሔራዊ ከፍታ እንዲውሉ አድርጓል።
የኢትዮጵያን ባህል፣ ታሪካዊ እሴቶች እና ባህላዊ ሀብቶች ለማዳበር፣ ለመንከባከብ እና ለትውልድ ለማስተላለፍ የተለያዩ ስራዎችን አከናውኗል።
የህዝቦችን ማህበራዊ ትስስር ለማጠናከር፣ ሀገር በቀል ዕውቀቶችን በመሰነድና በማስተዋወቅ አብሮነትን እና መቻቻልን ማጎልበት ተችሏል።
ታሪካዊ ቅርስና መዳረሻዎችን በመገንባት እና በማስተዋወቅ የኢትዮጵያን ታሪክ፣ መታሰቢያዎች እና የባህል ቱሪዝም በማሳደግ ረገድ ትልቅ ስራ ተሰርቷል፡፡
ይህ ሂደት በኢትዮጵያውያን መካከል ያለውን መተማመን እና አብሮነት ከፍ አድርጎታል። የህብረተሰቡን ሰላም፣ እርቅ እና የጋራ መከባበር እሴቶች ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋገሩና በዘመናዊ አሰራር እንዲዳበሩ የማድረግ ስራዎች ተከናውኗል።
የመደመር መንግሥት ባህልን ከማሳደግ አንጻር ያደረጋቸው ጥረቶች ብዝሃነትን በሃብትነት እስከ መጠቀም የዘለቁ ናቸው።
ይህ አካሄድ የህብረተሰቡን ማህበራዊ ትስስር በማጠናከር በኩል አበረታች ጅምሮችን ያስመዘገበ ሲሆን፤ ወደፊትም የሀገር በቀል እሴቶችን እና የታሪክ መዳረሻዎችን ይበልጥ በማስፋፋት ዘላቂ ብልጽግናን ለማረጋገጥ መሰረት የሚጥል ነው።
በከተሞች የተከናወኑት የኮሪደር ልማት ሥራዎች የታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶችን ገጽታ በጠበቀና በደመቀ መልኩ እንዲታዩ አድርገዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን ባህላቸውን፣ ቋንቋቸውንና እሴቶቻቸውን የሚያሳዩባቸው ብሔራዊ የባህል ፌስቲቫሎች እና የጎዳና ላይ በዓላት በጋራና በድምቀት እንዲከበሩ አድርጓል፡፡ ይህ በዓላቱ የቱሪዝም እና የሰላም መድረክ እንዲሆኑ አድርጓል።
በአጠቃላይ የመደመር መንግሥት ባህልን የሀገር መታወቂያ ብቻ ሳይሆን የልማት፣ የሰላምና የትውልድ ግንባታ መሳሪያ አድርጎታል።
በትዕግስት ግዛቸው

17 days ago