ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታጠቀው የኢትዮጵያ አየር ኃይል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል በቅርብ ዓመታት ያካሄዳቸው አጠቃላይ የመዋቅርና የቴክኖሎጂ ሽግግሮች፤ የቀጣናውን የኃይል ሚዛን የሚያስጠብቅ ግዙፍና ዘመናዊ ተቋም አድርጎታል።
ተቋሙ ከአናሎግ አሰራር ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ በመሸጋገር፤ እንደ Su-30 እና J-10 ያሉ አራተኛ ትውልድ ተዋጊ ጄቶችን፣ ዘመናዊ የሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና የራዳር ሥርዓቶችን በብቃት በማቀናጀት ኢትዮጵያን ከማንኛውም የደህንነት ስጋት የመጠበቅ አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ አሳድጓል።
ይህ የቴክኖሎጂ ሽግግር አየር ኃይሉ ማንኛውንም ሥጋት ቀድሞ የመከልከል እንዲሁም የሀገሪቱን ሉዓላዊነት፣ የሕዝቦቿን ሰላምና ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት አስተማማኝ በሆነ መንገድ የማስጠበቅ ስትራቴጂካዊ ብቃት እንዲኖረው አድርጎታል።
የኢትዮጵያ አየር ኃይልን በቀጣናው ካሉ መስል ተቋማት ተጽዕኖ ፈጣሪ የሚያደርገው የራሱን የጥገና፣ የማሻሻልና የማምረት አቅም መገንባቱ ነው።
ተቋሙ በምርምር ደረጃ የነበሩ የቴክኖሎጂ እውቀቶችን ወደ ተግባራዊነት በመቀየር፣ አውሮፕላኖችንና የሰው አልባ አውሮፕላኖችን በሀገር ውስጥ ከመጠገንና ከማሻሻል አልፎ፤ በቀን በመቶዎች የሚቆጠሩ መለዋወጫ ክፍሎችን በማምረት የውጭ ጥገኝነትን በዘላቂነት ማስወገድ ችሏል።
ይህም የተቋሙን ፍላጎት ከመሸፈን ባለፈ፤ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት የቴክኒክ ጥገና፣ የዕውቀት ሽግግርና የሙያ ሥልጠና ፍላጎታቸውን በኢትዮጵያ አየር ኃይል በኩል እንዲያሟሉ መንገድ ከፍቷል፡፡
በዚህም ተቋሙ የሀገር ውስጥ የመከላከያ ምሰሶ ከመሆን አልፎ የቀጣናው የቴክኖሎጂና የሥልጠና ማዕከል ለመሆን በቅቷል።
አየር ኃይሉ እስከ ፈረንጆቹ 2030 አሁን ያለውን የቴክኖሎጂና የውጊያ አቅም በእጥፍ ለማሳደግ እንዲሁም ወደ አምስተኛ ትውልድ የውጊያ ደረጃ ለማሸጋገር የተቀረጸውን ግልጽ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ወደ ተግባር እየቀየረ ይገኛል።
የሰው ኃይል ልማትን ከዘመናዊ የጦር ቴክኖሎጂ ጋር አጣጥሞ በመምራት ላይ የሚገኘው ተቋሙ፤ በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ሰላምና ደኅንነት ለማስከበር የማይተካ አህጉራዊ ሚና በመጫወት ላይ ነው።
በአጠቃላይ በቴክኖሎጂ፣ በሰው ኃይል እና በሀገር በቀል የማምረት አቅም ላይ የተገነባው ይህ ዘመናዊ አየር ኃይል፤ ኢትዮጵያ በቀጣናው የምትታወቅበትን ስትራቴጂካዊ የበላይነትና የሰላም አለኝታነት በግልጽ ያበሰረ ነው።
በአብረሃም አበራ

17 days ago