ኪነጥበብ፤ የሀገር ግንባታ ረቂቅ ኃይል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ብዙ ጊዜ ዕድገት ሲባል አዕምሯችን በቀጥታ የሚስለው የህንጻዎችን ግንባታ፣ ዘመናዊ የአስፋልት መንገዶችን ወይም የፋብሪካዎችን መስፋፋት ነው።
በርግጥ እነዚህ ልማቶች የሀገር መሰረት ናቸው፤ ነገር ግን የህዝብን መንፈስ፣ ማህበራዊ ትስስርና ስብዕና የሚገነባው ከእነዚህ መሰረተ ልማቶች ጎን ለጎን ጥበብም ጭምር ነው።
ኪነጥበብ የማህበረሰቡ የህሊና ውቅር፣ የትናንት መዝገብ፣ የዛሬ መስታዎትና የነገ አቅጣጫ ጠቋሚ አመላካች ነው:: ሙዚቃ፤ ቴአትር፣ ሥነ-ጽሑፍና ሥዕል ድንበርና ቋንቋን ተሻግረው የሰዎችን ልብ የማገናኘት ተፈጥሯዊ ኃይል አላቸው።
ኢትዮጵያ በረጅም ዘመናት የታሪክ ጉዞዋ በኪነጥበብ፣ በባህልና በቅርስ የበለጸገች ሀገር ብትሆንም፤ ጥበብን ከሀገር ዕድገት ጋር አስተሳስሮ የመመልከት ልምዳችን ገና በጅምር ደረጃ ይገኛል።
ሆኖም በቅርብ ዓመታት መንግሥት ለዘርፉ እየሰጠ ያለው ትኩረት እና የፖሊሲ አቅጣጫ ለኪነጥበብ ዕድገት አዲስ ተስፋ ፈንጥቋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የፈጠራ ኢኮኖሚ የሚባለው ይህ ዘርፍ ቢሊየን ዶላሮችን የሚያንቀሳቅስና ለሚሊየኖች የሥራ ዕድል የሚፈጥር ታላቅ ኢንዱስትሪ ነው።
ኢትዮጵያ በወጣት ማህበረሰብ ቁጥር የታደለች ሀገር እንደመሆኗ፤ ይህ ዘርፍ የፈጠራ ክህሎትን ለማዳበር እና የስራ አጥነትን ችግር ለመቅረፍ ትልቅ አቅም አለው።
ከዚህ ቀደም ኪነጥበብ እንደ አንድ የመዝናኛ ወይም የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ ተደርጎ የመታየት አዝማሚያ የነበረው ቢሆንም፤ በአሁኑ ወቅት ግን መንግሥት ዘርፉን በሀገራዊ የልማትና የዕድገት ስትራቴጂ ውስጥ እንደ አንድ ዋና አምድ አድርጎ መመልከት ጀምሯል።
በቅርብ ጊዜያት እውን በመሆን ላይ ያሉት ዘመናዊ የኪነጥበብና የባህል ማዕከላት፣ ቤተ-መጻሕፍት፣ ሙዚየሞች እና የታሪክ መዘክሮች ግንባታ ለጥበብ ስራዎች ትልቅ መድረክ ከፍተዋል።
እነዚህ መሰረተ ልማቶች የጥበብ ባለሙያዎች ስራቸውን እንዲያቀርቡ ብቻ ሳይሆን፤ ህብረተሰቡ የጥበብ ባህልን እንዲያዳብርና ለቱሪዝም ሳቢ ስፍራዎች እንዲሆኑም አድርገዋል።
አንዲት ሀገር በዓለም አቀፍ መድረክ የሚኖራት ስምና ገጽታ ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ዕድገት ወሳኝ ነው።
ኢትዮጵያ የድንቅ ታሪክና የባህል ባለቤት ብትሆንም፤ በዓለም ፊት፣ በውጭ ሚዲያዎች ሲነገሩ በቆዩ አሉታዊ ትረካዎች ስትነሳ ቆይታለች። ይህንን የተዛባ ምስል የመቀየር ኃይል ያለው ደግሞ ከኢኮኖሚ እድገትና ብልጽግና በተጨማሪ የባህል ዲፕሎማሲ እና ኪነጥበብ ነው።
በዚህም በቅርቡ የኢትዮጵያን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የሚወክሉ በርካታ የኪነጥበብ ቡድኖች በተለያዩ የዓለም ሀገራት በመጓዝ ሀገራቸውን የሚያስተዋውቁባቸው መድረኮችን መመልከት የተለመደ እየሆነ መጥቷል፡፡
መንግሥት የኢትዮጵያን ባህልና ጥበብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ የሚያደርጋቸው ጥረቶች፤ የባህል ቡድኖችን መላክ፣ በዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽኖች ላይ መሳተፍ እና የፊልም ኢንዱስትሪውን ማበረታታት የሀገሪቱን ውበትና ትክክለኛ መልክ በተገቢው መንገድ ይገልጣሉ። ይህም የቱሪስቶችን ቀልብ በመሳብ የቱሪዝም ዘርፉን ያነቃቃል።
እነዚህ የተቀናጁ ጥረቶች ኪነጥበብ የኢትዮጵያ ሁለገብ ዕድገት አካል ሆኖ እንዲቀጥል መሰረት ይጥላሉ።
ኪነጥበብ የሕዝብን መንፈስ የሚያነቃቃ፣ የፈጠራ አቅምን ወደ ኢኮኖሚ ሀብት የሚቀይርና የሀገርን መልካም ገጽታ በዓለም አቀፍ መድረክ የሚያጎላ ረቂቅ ኃይል ነው::
መንግሥት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት አጠናክሮ በመቀጠል፤ ከጥበብ ባለሙያዎች፣ ከግል ባለሃብቶችና ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት የሚያደርገው ጥረት ለኪነጥበብ ህዳሴ ወሳኝ አቅም ይፈጥራል።
ዛሬ በጥበብና በባህል ላይ የምናደርገው ኢንቨስትመንት፣ ለነገ የሚገነባውን ትውልድ ስብዕና የሚያንጽና የሀገራችንን ሁለገብ ብልጽግና የሚያረጋግጥ ዘላቂ እሴት ነው::
በመልካም ፈቃዱ

18 days ago