የሐረር ከተማን ተመራጭ የቱሪስት መዳረሻ የሚያደርግ ስራ ተሰርቷል - አቶ ቴዎድሮስ ምህረት
*******************
የሐረር ከተማን የቱሪዝም ሳቢነት ከፍ ለማድረግና ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ የሚከናወኑ የልማት ተግባራት ተስፋ ሰጪ ውጤት እያሳዩ መሆናቸውን የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት ገለጹ።
በአቶ ቴዎድሮስ ምህረት የተመራና የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንቶችን እንዲሁም የሐረሪ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ያካተተ ከፍተኛ ልዑክ በሐረር ከተማ የሚገኙ የተለያዩ የቱሪስት መስህቦችንና አዲስ የተገነባውን የጅብ ትርዒት ማሳያ ኢኮ ፓርክን ጎብኝቷል።
በጉብኝቱ ወቅት አቶ ቴዎድሮስ እንደተናገሩት፤ በከተማዋ የተገነባው የጅብ ትርዒት ማሳያ ኢኮ ፓርክ የክልሉን የቱሪዝም አቅም በከፍተኛ ደረጃ የሚያጎለብትና ለጎብኚዎች ምቹ ሁኔታን የፈጠረ የልማት አውታር ነው።
አክለውም በክልሉ የቱሪዝም መስህቦችን ለማስፋፋትና ለማዘመን የተከናወኑ አበራች ጥረቶች አዎንታዊ ውጤት ማስመዝገባቸውን ጠቁመው፣ መሰል የመሰረተ ልማት ዝርግያዎች ከተማዋን ተመራጭ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የሚደረገውን ጉዞ እንደሚያፋጥኑት ገልጸዋል።

18 days ago