የአንድነትና የምስጋና ድምፅ፣ «ኢሬቻ አንድነት ኮንሰርት» መስከረም 22 ሊካሄድ ነው
በኢትዮጵያ የባህልና የኪነ-ጥበብ መድረክ ላይ ደማቅ አሻራውን ያሳረፈው የኢሬቻ በዓል ዋዜማን ምክንያት በማድረግ «ኢሬቻ አንድነት ኮንሰርት» (Irreecha Unity Concert) ሊካሄድ መሆኑ ተነገረ።
በመሰረት ዳባ ኢቨንት ኤንድ ፕሮሞሽን አዘጋጅነት የሚካሄደው ይህ ታላቅ የሙዚቃና የባህል ምሽት፣ መስከረም 22 ቀን ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ በሁለት የተለያዩ ቦታዎች—አራዳ ፓርክ ናፍሌት ሆቴል እና ስካይላይት—በደማቅ ሁኔታ እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን፣ አዘጋጆቹ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የዝግጅቱን ዝርዝር ሁኔታዎች ይፋ አድርገዋል።
የዝግጅቱ ዋነኛ ዓላማ የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የምስጋና፣ የሰላም፣ የፍቅርና የመተሳሰብ መልእክቶችን በኪነ-ጥበብና በሙዚቃ አወሃህዶ ማቅረብ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፤ የኢሬቻ በዓል የኦሮሞ ህዝብ ባህል ብቻ ሳይሆን የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች የጋራ የምስጋናና የአንድነት መድረክ መሆኑን ማሳየት ነው።
በዚህ ታላቅ ኮንሰርት ላይ ገላና ጋሮምሳ፣ ሐመልማል አባተ ፣ ጃምቦ ጆቴ ፣አደም መሀመድ ፣ጌታቸው ሐ/ማርያም ፣ አሳንቲ አስቹ ፣ሹክሪ ጀማል ፣ ገዳ ሐምዳ እና ሌሎችም ወጣት እና አንጋፋ ከአስር በላይ አርቲስቶች ስራቸውን ያቀርባሉ።
እንዲሁም ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ማለትም ከሐረሪ፣ ከሲዳማ፣ ከሶማሌ እና ከአፋር የሚጡ ወጣቶች የተጋበዙ ሲሆን የኢሬቻ በዓልን ምንነት በሚገባ እንዲያውቁ መልካም እድል ተመቻችቷል።
የመሰረት ዳባ ኢቨንት ኤንድ ፕሮሞሽን መስራችና ስራ አስኪያጅ መስረተ ዳባ በሰጡት ቃል፣ መላው የአዲስ አበባ ህዝብ፣ ኦሮሞ ማለት የሰላምና የመልካምነት ምልክት መሆኑን ተረድቶ፤ በዚህ የአንድነትና የደስታ ምሽት ላይ ታድሞ አብሮ እንዲያከብርና እንዲዝናና ጥሪ አቅርበዋል።
የኮንሰርቱ ትኬቶች በናፍሌትና በስካይላይት ሆቴሎች ከማግኘት ባለፈ በቅርቡ ''jirtu'' ''ጅርቱ'' በተሰኘው የሞባይል አፕሊኬሽንና በቴሌብር አማካኝነት በቀላሉ መግዛት እንደሚቻል ተገልጿል።
የትኬት እና ተያያዥ መረጃዎች በድርጅቱ እና በሌሎች ማህበራዊ ድረ ገጾች የሚገለጹ ይሆናል።
📸 ከበደ መክብብ

19 days ago