(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) የዓለም ቆንጆ የውበት ውድድር ላይ ኤርትራን ለመጀመሪያ ጊዜ በመወከል ታሪክ የሠራችው ስኒት ሃብተአብ፣ ውድድሩን አስመልክታ ስሜት ኮርኳሪ የሆነ የጽሑፍ መልእክት አስተላልፋለች። ስኒት ባጋራችው በዚህ መልእክት "ይህንን ለመጻፍ ጥቂት ጊዜ ወስዶብኛል፣ ምክንያቱም የተሰማኝን ሁሉ በውስጤ ማሰላሰል ፈልጌ ነበር" በማለት የጀመረች ሲሆን፣ ጠቅላላ ጉዞዋን ግን "ምስጋና" በሚለው አንዲት ቃል እንደምትገልጸው አስታውቃለች።
"የዓለም ቆንጆ ውድድር የመጨረሻዬ ነው፤ ውበትን ከሚታየው ገጽታ ባለፈ ለማንነትሽ፣ ለምታራምጅው አቋምሽ እና ለዓለም ለምታበረክችው ነገር ዕውቅና በሚሰጥ መድረክ ላይ ይህንን ምዕራፍ መዝጋቴ እጅግ ትርጉም ያለው ነው" በማለት ስኒት ገልጻለች። ኤርትራ ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፈችበት በዚህ መድረክ፣ ስኒት ከፊት-ለፊት በነበረው ፉክክር (Head-to-Head) ምርጥ 5፣ እንዲሁም በተሰጥኦ ውድድር ምርጥ 23 ውስጥ መግባት ችላለች። ነገር ግን ወደ ምርጥ 40 እና በመጨረሻም ወደ ምርጥ 6 እንድትገባ ያደረጋት የኤርትራውያን ታላቅ ድጋፍ መሆኑን አስታውሳለች።
"አንዳንዶች የድምጽ አሰጣጡን አይተው ገንዘብ ከፍዬ ያለፍኩ ሊመስላቸው ይችላል፤ ነገር ግን ያላዩት እውነት ቢኖር ሌሊት እንቅልፍ አጥተው ነፃ የድምጽ መስጫ ዕድሎችን ሲጠቀሙ የነበሩትን፣ በእጥፍ የሚሰላበትን ጊዜ ሲጠብቁ የነበሩትን እና እስከ መጨረሻው ሰዓት ድረስ ለድምጽ አሰጣጥ ሲቀሰቅሱ የነበሩትን ሰዎች ነው" ስትል የሀገር ልጆቿን ትጋት አድንቃለች። ሰዎች "ኤርትራ ምን ያህል ትልቅ ናት? ይህ ሁሉ ድጋፍ ከየት ነው የሚመጣው?" ብለው ሲጠይቁ እንደነበርም የገለጸችው ስኒት፣ "በቁጥር መግለጽ የማይቻለውን፣ ድንበር እና ልዩነትን ያሸነፈውን የኤርትራውያንን አንድነት ዓለም እንዲያየው አድርጋችኋል፤ ይሄ በገንዘብ ሊገዛ የማይችል ነው" ስትል ኩራቷን ገልጻለች።
በውድድሩ ላይ ስለለበሰችው ውብ ልብስም ስትናገ "በኤርትራ ቀይ ባሕር ጥልቀት ተመስጦ የተሠራው ይህ የንጉሣዊ ሰማያዊ ቀለም ልብስ፣ ልክ እንደ ሀገሬው ሰዎች ባሕልና እሴት ጠለቅ ብለህ በገባህ ቁጥር ውበቱ ጎልቶ የሚታየውን የኤርትራን ገጽታ የሚወክል ነው" በማለት ንድፍ አውጪውን ኢየሱስ ቪሽኒቬትስኪይን አመስግናለች።
ስኒት ሃብተአብ በመጨረሻም ስትሰናበት "ይህንን ምዕራፍ ስዘጋው፣ ይዤው ስላልመጣሁት ዘውድ እያሰብኩ ሳይሆን፣ ይዘን ስለመጣነው ታሪክ፣ እውቅና፣ አንድነት እና ለቀጣይ ሴቶች ስለከፈትነው በር እያሰብኩ ነው" ብላለች። የልጅቷ ጉዞ ከውበት ውድድርነትም ባለፈ አንድ አነስተኛ ሕዝብ ያላት ሀገር፣ ዜጎቿ በተባበሩ ቁጥር በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ምን ያህል ትልቅ ድምጽ እና ተጽዕኖ መፍጠር እንደሚችሉ በተጨባጭ ያሳየችበት ነው። የሀገር ፍቅርን፣ አንድነትን እና ኩራትን ለዓለም በማሳየት፣ ስኒት ሃብተአብ የኤርትራን ስም በክብር አስጠርታለች።

20 days ago