ኡጋንዳ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ድጋፏን እንደምትቀጥል አረጋገጠች
የኡጋንዳዋ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄሲካ አሉፖ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሀገሪቱ በምታደርገው የማስፋፋት ሥራ መንግሥታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
ድጋፉ የተገለጸው የቤተክርስቲያኗ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና በኡጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር ከምክትል ፕሬዝዳንቷ ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ነው። በስብሰባው ወቅት የቤተክርስቲያኗ ተወካዮች የኡጋንዳ መንግሥት ለስደተኞች፣ ለሃይማኖት ነፃነትና ለቤተክርስቲያኗ እድገት ላደረገው እገዛ ምስጋና በማቅረብ የተጀመረው አጋርነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
ምክትል ፕሬዝዳንቷ በበኩላቸው፤ የሃይማኖት ተቋማት ለሀገርና ለሕዝብ ሰላም ያላቸውን ሚና አጉልተው አሳይተዋል። የጸሎት ሥነ ሥርዓቶች ምንም ዓይነት እንቅፋት ሳይገጥማቸው እንዲከናወኑና የቤተክርስቲያኗ የማስፋፋት ሥራዎች እንዲሳኩ መንግሥታቸው አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
Seledadotio

20 days ago