Logo
SeledaPost
ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚያወጡ 17 ከብቶችን በአንድ ጊዜ የሰረቀው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ::

በምስራቅ ጎጃም ዞን አዋበል ወረዳ 17 የቀንድ ከብቶችን የሠረቀው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን ፖሊስ አስታውቋል።ተከሳሽ መርሻ ደምሴ የአዋበል ወረዳ ነዋሪ ሲሆን ዱቄ ቀበሌ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ በአንዴ 17 ከብቶችን ሠርቆ ሲነዳ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።
 
ተከሣሹ የ1 ሚሊዮን 47 ሺህ ብር የዋጋ ግምት ያላቸውን 17 የቀንድ ከብቶች መስረቁ ተገልጿል።ተከሳሹ የሰረቃቸውን ከብቶች ወደ ደጀን ወረዳ በማዘዋወር ለመሸጥ በእንቅስቃሴ ላይ እያለ በደጀን ወረዳ የጸጥታ ኃይሎች በተደረገ ክትትል ጢቅ ቀበሌ ቁልቋል አካባቢ በቁጥጥር ስር መዋሉ ታውቋል ።

የደጀን ወረዳ የጸጥታ ኃይሎች ተጠርጣሪውን እና ከብቶቹን ለወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስረክበዋል። ፖሊስም ምርመራውን አጠናቅሮ መዝገቡን ለአቃቤ ሕግ በማቅረብ ክስ ተመስርቶበታል ።
 
የደጀን ወረዳ ፍርድ ቤትም ተከሳሹን በስርቆት ወንጀል ጥፋተኛነቱን ካረጋገጠ በኋላ በ4 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

የቅጣቱ ዓላማ ተከሳሹን ለማረም እና ሌሎችንም ከተመሳሳይ ወንጀል እንዲቆጠቡ ለማስተማር መሆኑን የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ መግለፁን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።

Seledadotio
Seledadotio
21 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.