በብሪክስ በጽኑ ድጋፍ ያገኘው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሒደትና ሌሎች ስኬቶች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በሕንድ ኒው ዴልሒ በተካሄደው 18ኛው የብሪክስ መሪዎች ጉባዔ ያሳየችው ንቁ ተሳትፎ የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ እድሎችን ያሰፋ ውጤት አስገኝቷል።
በጉባዔው ለኢትዮጵያ የተሰጡ ድጋፎች እና ከመርሐ ግብሩ ጎን ለጎን የተካሄዱ የሁለትዮሽ ውይይቶች የሀገሪቱን የዲፕሎማሲ ተሳትፎ ያጠናከሩ ናቸው።
በብሪክስ መድረክ የዓለም አቀፍ ንግድ፣ የአየር ትራንስፖርትና የአየር ንብረት ጉዳዮች መነሳታቸው ኢትዮጵያ በቀጣይ ዓመታት በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ሚና ለማጠናከር ዕድል ፈጥሯል።
ከጉባዔው ጉልህ ውጤቶች መካከል የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሒደት የብሪክስ ድጋፍ ማግኘቱ አንዱ ነው።
ይህ ኢትዮጵያ ወደ ዓለም አቀፉ የንግድ ሥርዓት በተሻለ ሁኔታ ለመቀላቀል እያካሄደች ላለው ሒደት ተጨማሪ ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ያስገኛል።
ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሒደቷን ለማፋጠን ከዓለም አቀፍ ገበያ ጋር ያላትን ትስስር ማስፋት፣ የውጭ ኢንቨስትመንትን መሳብና የምርቶቿን ወደ ዓለም ገበያ የማቅረብ አቅም ለማሳደግ እየሰራች ትገኛለች።
በዚህ ሒደት ውስጥ የብሪክስ ድጋፍ የኢትዮጵያን የድርድር አቅም የሚያጠናክር ዲፕሎማሲያዊ ውጤት ሆኗል።
ሌላው በጉባዔው የተጠናከረው ጉዳይ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ተቋማት የተሻለ ውክልና እንዲኖራት እያደረገች ያለው ጥረት ነው።
ብሪክስ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ም/ቤት ለተጨማሪ ወንበር ያቀረበችውን እጩነት በመደገፍ፣ በዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ውሳኔ ሰጪ መድረክ የአፍሪካ ድምፅ እንዲጠናከር ያለውን ፍላጎት አሳይቷል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት የተደገፈች ብቸኛዋ የአፍሪካ እጩ መሆኗንም ብሪክስ በጋራ መግለጫው ጠቅሷል። ይህ ድጋፍ ኢትዮጵያ ከአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ጋር በተያያዘ ካላት ልምድና አቅም ባሻገር፣ በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ተቋማት የፖሊሲ ተሳትፎዋን ለማሳደግ የምታደርገውን ጥረት የሚያጎላ ነው።
ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ልታስተናግድ ለተዘጋጀችው 32ኛው የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (ኮፕ32) የብሪክስን ድጋፍ ማግኘቷም ሌላው ጉልህ የዲፕሎማሲ ውጤት ነው።
ይህ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ተሞክሮዋን ለዓለም ለማቅረብ እና የአፍሪካ የአየር ንብረት፣ ፋይናንስና ልማት ፍላጎቶችን በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስገንዘብ ወሳኝ እድል ይፈጥራል።
የብሪክስ ጉባዔ የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ አቅም ያሳየ ወሳኝ መድረክ ሲሆን ÷ ከጉባዔው ጎን ለጎን የተካሄዱት የሁለትዮሽ ውይይቶችም እኩል ትኩረት የሚሹ ናቸው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከብሪክስ አባልና ከአጋር ሀገራት መሪዎች ጋር ባደረጓቸው ውይይቶች የንግድ፣ የኢንቨስትመንት፣ የቴክኖሎጂ፣ የዲጂታል ለውጥ፣ የመከላከያ፣ የማዕድን፣ የቱሪዝምና የአቅም ግንባታ ጉዳዮች በትኩረት ተነስተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በብሪክስ መድረክ የአፍሪካ ተሳትፎ እንዲጠናከር፣ የፋይናንስና የገበያ ተደራሽነት እንዲሰፋ እና የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የክልላዊ ትስስር ተግባራዊ ትብብር እንዲጠናከር ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ በተጨማሪም የብሪክስ አዲስ ልማት ባንክ በአፍሪካ ያለውን ተደራሽነት ለማስፋት በአዲስ አበባ ቢሮ ለመክፈት ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች።
ይህ ተግባራዊ ከሆነ የአፍሪካ ሀገራት የልማት ፋይናንስ ተደራሽነትን ለማሳደግ እና አዲስ የኢንቨስትመንት አጋርነቶችን ለመፍጠር ያግዛል።
ከዚህ ባሻገር፣ በጉባዔው ጎን ለጎን የተካሄዱ የሁለትዮሽ ውይይቶች ከንግድና ኢንቨስትመንት እስከ ቴክኖሎጂ፣ መከላከያና ማዕድን ድረስ ባሉ ዘርፎች የተግባር ትብብር ለማስፋት አዲስ የዲፕሎማሲ መስኮቶችን ከፍተዋል።
በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በኒው ዴልሒ ያሳየችው ተሳትፎ የብሪክስ አባልነቷን ከዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎ ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ፣ የንግድ፣ የቴክኖሎጂና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተሳትፎ ለመቀየር ያላትን ዕድል ያሳየ ነው።

23 days ago