ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለአንድ የማስታወቂያ ጽሑፍ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ያስከፍላል
#ethiopia | በእግር ኳሱ ዓለም ያላቸው ፉክክርና ዝና ወደ ማኅበራዊ ትስስር ገጾችም ተሻግሮ፣ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ሊዮኔል ሜሲ በገቢያቸውም ውድድር ጀምረዋል።
ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአንድ የኢንስታግራም የማስተዋወቂያ ጽሑፍ ብቻ 3.2 ሚሊዮን ዶላር በማግኘት በዓለም ከፍተኛ ተከፋይ ስፖርተኛ ሆኖ በግንባር ቀደምትነት እየመራ ይገኛል።
ይህ አስገራሚ ገቢው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ያለውን ግዙፍ ተደራሽነትና ተጽዕኖ በግልጽ ያሳያል።
በእግር ኳስ ሜዳው ላይ ሁሌም የሚፎካከረው አርጀንቲናዊው ሊዮኔል ሜሲ ደግሞ በአንድ ጽሑፍ 2.7 ሚሊዮን ዶላር በማግኘት በቅርብ ርቀት ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
ሁለቱ የእግር ኳስ ታላላቅ ተጫዋቾች (GOATs) በሜዳ ላይ ከሚያሳዩት ድንቅ ብቃት በተጨማሪ፣ ከሜዳ ውጪ ባለው የዲጂታል ገበያም ከፍተኛውን ገቢ በመሰብሰብ የበላይ ናቸው ።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

24 days ago