የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ፡ ከነፃነት ዓርዓያነት ወደ ዘመናዊ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ታሪክ የነፃነትና የሉዓላዊነት ምልክት ከመሆን አልፎ የአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት ምስረታ ግንባር ቀደም መሃንዲስ በመሆን የተገነባ የጸና መሠረት አለው።
በዓለም አቀፍ መድረኮች የጥቁር ህዝቦች ድምፅ ሆና በመቆም አያሌ ታሪካዊ ኃላፊነቶችን የተወጣችው ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ ያንን የጽኑ ዲፕሎማሲ ቅርሷን ወደ ዘመናዊ የኢኮኖሚ ብልጽግና እና ሁለንተናዊ አጋርነት በመቀየር አዲስ ምዕራፍ ጀምራለች።
ሀገሪቱ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ የሕዝቧን የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን እና ቀጣይነት ያለው ዕድገቷን ለማረጋገጥ ከዓለም ሀገራትና ተቋማት ጋር የምታደርገውን ዲፕሎማሲያዊ ትስስር አጠናክራ ቀጥላለች።
በዚህ ረገድ የለውጡ መንግስት ካከናወናቸው ታሪካዊና ስትራቴጂካዊ የዲፕሎማሲ ጥረቶች አንዱ ሀገሪቱን በ2016 የብሪክስ አባል እንድትሆን ማስቻል በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።
ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ የታሪካዊ ተደማጭነቷን ማረጋገጫ ብቻ ሳይሆን ወደ ፋይናንስ፣ ኢንቨስትመንትና የመሰረተ ልማት ትብብር የተደረገ ትልቅ ዕመርታ ነው።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆኑ እና የዓለምን 48 በመቶ ሕዝብ የሚወክሉ ሀገራት ስብስብ አካል መሆኗ ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ድምጿ እንዲሰማና ሰፊው ኢኮኖሚያዊ ጥቅሟ እንዲከበር ያስችላል።
በተለይም ጉባዔው “ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት” በሚል መሪ ሃሳብ በኒው ዴልሂ መካሄድ በጀመረው 18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባዔ ላይም ኢትዮጵያ የምታደርገው ተሳትፎ አንድምታው ትልቅ ነው።
ይህ አዲሱ የዲፕሎማሲ አቅጣጫ ለኢትዮጵያ በርካታ ተጨባጭ ዕድሎችን ይዞ የመጣ ሲሆን የኒው ዲቨሎፕመንት ባንክ አባልነት ረቂቅ አዋጅ መጸደቁም ለሀገራዊ ልማትና መሰረተ ልማት ግንባታ የሚረዱ አማራጭ የፋይናንስ ምንጮችን ለማግኘት ያስችላል።
በተጨማሪም በስብስቡ ጥላ ስር ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች በስራ ፈጠራ፣ በቴክኖሎጂ፣ በጤና እና በትምህርት መስኮች የተከፈቱት ዓለም አቀፍ ትስስሮች የወደፊት የልማት ተስፋዎችን የሚያመለክቱ ናቸው።
ኢትዮጵያ በታሪኳ የገነባችውን የዲፕሎማሲ ስኬት ዛሬ ላይ ከፍትሃዊ፣ አሳታፊና አካታች የዓለም አቀፍ የትብብር መርሆች ጋር በማጣመር እየተጠቀመችበት ትገኛለች።
የብሪክስ አባልነት ያመጣቸውን የንግድ፣ የቱሪዝም እና የቴክኖሎጂ ዕድሎች ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም የመንግሥት ተቋማት፣ የንግዱ ማህበረሰብ እና ወጣቶች በጋራ ሊሰሩ ይገባል።
ኢትዮጵያ በልማታዊ መርህ የሚመራ የዲፕሎማሲ መሪነቷን በማጠናከር፣ ታሪካዊ የነፃነት ተምሳሌትነቷን ወደ ዘመናዊ የኢኮኖሚ ብልጽግና በመቀየር ላይ ትገኛለች።
በዮናስ ጌትነት

25 days ago