Logo
Tigu S Alemayew
መልካም አዲስ ዓመት።

በጎጆ የህሙማን ማረፊያ የበጎ ፍቃደኝነት ጉብኝት እንደቀጠለ ነው...
እንደተለመደው የአዲስ ዓመት የዘመን መለወጫን (የእንቁጣጣሽ) በዓልን በማስመልከት የዘወትር የማረፊያው ቤተሰብ ቤሩት(መሠረት) እና ቤተሰቦቿ የሙስሊም እና የክርስቲያን በጎችን በመግዛት በህሙማኑ ማረፊያ በመገኝት በዓሉን በማዘጋጀት፣ አቶ ፍቃዱ ጣፋ እና ቤተሰቦቹ 240 እንቁላል ለበዓሉ በማበርከት እንዲሁም ትጉ እና ባለቤቷ ለመቶ ሰው የሚሆን የሙስሊም እና የክርስቲያን ምግብ,በማቅረብ፣ የቡና ሴሬሞኒምውን በማዘጋጀት ከህሙማኑ ጋር በዓሉን በዚህ ሁኔታ አሳልፈዋል።
ቤሩት(መሠረት)ን እና ቤተሰቦቿን፣ ትጉ እና ባለቤቷን እንዲሁም አቶ ፍቃዱ ጣፋ እና ቤተሰቦቹን እያመሰገንን መላው የማረፊያው ቤተሰብን መልካም አዲስ ዓመት ይሁንላቹ እንላለን።

የማረፊያው ተጠቃሚ ህሙማንን እንዲሁም ሌሎችም ወገኖች በመተሳሰብ እና በመረዳዳት ባለንበት እንኑር እንላለን።

25 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.