Logo
Ethio telecom
ጳጉሜን 5 “የነገ ቀን” በሳይንስ ሙዚየም በድምቀት ተከበረ

በዲጂታል የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመገንባት የተከናወኑ ስኬቶችና በቀጣይ የሚሠሩ ሥራዎች የተዳሰሱበት ጳጉሜን 5 “የነገ ቀን” መርሃ ግብር በአውደ-ርዕይ እና በፓናል ውይይት በሳይንስ ሙዚየም በድምቀት ተከብሯል።

የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በመርሃ ግብሩ ላይ፤ “ለእኛ 'ዲጂታል ኢትዮጵያ' ስንል በቴክኖሎጂ ፋንታሲ የሚደረግ ጉዞ ሳይሆን፣ ሰውን ማዕከል ያደረገ የዲጂታል ልማት ራዕይ ነው። ቴክኖሎጂ ትርጉም የሚኖረው ሰብአዊነትን አጎልብቶ ሁሉንም ዜጋ እኩል ተጠቃሚ ማድረግ ሲችል ነው” ብለዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን አክለውም፤ “በቀደሙት ጊዜያት የተፈጠሩ የዲጂታል ክፍተቶችን እያጠበብን፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈች፣ አካታችና ብልጽግናዋ የተረጋገጠች ሀገር ለመገንባት በቁርጠኝነት እንሰራለን” ሲሉ ገልጸዋል።

ኩባንያችን የቴሌኮም እና የዲጂታል መሠረተ ልማቶችን በስፋት በመገንባት፣ የ4ጂ እና የ5ጂ ኔትዎርክ ሽፋንን በማስፋፋት እንዲሁም የፋይበር ኔትዎርክ ዝርጋታን በማፋጠን ለሀገራችን የቴክኖሎጂ ሽግግር ከፍተኛ መደላድል በመፍጠር ላይ ይገኛል።

በተጨማሪም ወሳኝ የሆኑ የግብርና፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ቱሪዝም እና የማዕድን ዘርፎችን እንዲሁም በስማርት ሲቲ ግንባታ እና ቢዝነሶችን በዲጂታል ሶሉሽኖች በመደገፍ ለዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ ስኬት ጉልህ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።

ከዚህም ባሻገር የፋይናንስ አካታችነትን በማረጋገጥ፣ በቴሌብር አማካኝነት ከጥሬ ገንዘብ ነፃ የሆነ ኢኮኖሚ ከመፍጠር ባለፈ፤ ሀገራችንን የዲጂታል ሉዓላዊነት በሳይበር ሴኩሪቲ መስክ በማጠናከር ረገድ በርካታ ተግባራት አከናውኗል።

በቀጣይም የኢትዮጵያን የዲጂታል መጻኢ ዕድል በመቅረጽ እና የ“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030” ራዕይ እውን ለማድረግ ኩባንያችን የተጣለበትን ቁልፍ ተልዕኮውን በታላቅ ቁርጠኝነት ተግባራዊ ማድረጉን ይቀጥላል።
#ethiotelecom #telebirr #nexthorizon #realizingdigitalethiopia #digitalafrica

27 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.