Logo
YenetaTube
አዲስ አበባ በአዲስ ዓመት ከፋንታ ጋር እየደመቀች ነው!

ተወዳጁ ፋንታ እንደተለመደዉ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ጳጉሜ ወር በሙሉ በመዲናችን አዲስ አበባን ለማህበረሰባችን በነፃ ትራንስፖርት በመስጠት ላይ ይገኛል!

በዚህ ልዩ የበዓል ጉዞ በአውቶቢስ ውስጥ የተለያዩ የበዓል ሽልማቶችን እየሸለመ፣ በተለያዩ አዝናኝ ጨዋታዎች፣ ተሳፋሪዎች እያዝናና ከመነሻ እስከ መድረሻችሁ ጥርሳችሁን ሳትከድኑ እያደረሳችሁ ይገኛል። የትናችሁ ፒያሳ፣ መገናኛ፣ ሜክሲኮ፣ መርካቶ፣ ኮዬ፣ አያት፣ ሱሉልታ፣ ጣፎ፣ ጀሞ፣ ቃሊቲ እና ሌሎችም አካባቢዎች የሚደረገው ጉዞ ሙሉ በሙሉ ነፃ ከመሆኑም በላይ፣ በጨዋታዎቹ ለሚሳተፉ መንገደኞች ዶሮዎች፣ እንቁላል እና ሌሎችንም የበዓል ስጦታነት እያበረከተ ይገኛል።

በአውቶቡሱ ውስጥ ከታዋቂ ቲክቶከሮችና ኮሜዲያኖች ጋር በሚደረጉ ጨዋታዎችና ጥያቄዎች ጉዞዎን ያደምቁ! ፋንታ አሁንም “የት እንምጣ?” እያለዎት ነው፣ አውቶቡሱ ወደ ሰፈራችሁ እንዲመጣ የምትፈልጉበትን አካባቢ ኮመንት ላይ ጻፉልን፤ ያላችሁበት እንመጣለን።

መልካም አዲስ ዓመት! ከፋንታ ጋር በነፃ ይጓዙ፣ ይጫወቱ፣ ይሸለሙ!
#fantaethiopia #addisababa #fantafreetransportaddis #enkutatash2019 #fantabusactivation #ethiopiannewyear #fantagiveaway

28 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.