(ዘ-ሐበሻ ዜና) የሕክምና ወጪን መሸፈን አቅቷቸው ልጆቻቸው ሲሰቃዩባቸው ለነበሩ 60 እናቶች፣ ያለፉት ዘጠኝ ቀናት የጭንቀት ዘመናቸው አብቅቶ የደስታ እንባ ያነቡባቸው ነበሩ። ከአዲስ አበባ ርቀው ለሚገኙ የልብ ሕሙማን ሕፃናት የተዘረጋው የነፍስ አድን ዘመቻ በጅማ ከተማ በስኬት ተጀምሯል።
በHeart to Heart Children's Aid አስተባባሪነት፣ በአንድ ዓመት ውስጥ ለአንድ ሺህ ሕፃናት ነፃ የልብ ቀዶ ሕክምና ለመስጠት በተያዘው አብይ ዕቅድ መሰረት፣ የመጀመሪያው ዙር መርሐግብር በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል በስኬት ተጠናቋል። በዚህም በ9 ቀናት ውስጥ ብቻ ለ60 ሕፃናት ነፃ የልብ ቀዶ ሕክምና ተሰጥቷል።
በመርሐግብሩ ጅማ ሆስፒታል ውስጥ በነበረው የወረፋ ቅደም ተከተል መሰረት፣ በመጀመሪያ ለ200 ያህል ሕጻናት የልብ አልትራሳውንድ (Echo) ምርመራ የተደረገ ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ ለ60ዎቹ ነፃ የቀዶ ሕክምና ተሰጥቷል። ይህ ተግባር የሕፃናቱን ሕይወት ከመታደግ ባለፈ የእናቶችን እንባ በዘላቂነት ማበስ መቻሉ የዘመቻው ትልቁ ስኬት ተብሏል።
የኸርት ቱ ኸርት ቺልድረንስ ኤይድ መሥራችና የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ብርሃን ተድላ እንደገለጹት፣ ይህ የነፍስ አድን ሥራ በ2019 ዓ.ም ተጠናክሮ ይቀጥላል። በቀጣዩ ዓመት በ10 የተለያዩ የክልል ከተሞች በሚገኙ የመንግሥት ሆስፒታሎች ቀሪዎቹን 940 ሕፃናት በነፃ የማከሙ ተግባር እንደሚከናወን አረጋግጠዋል።
ይህ ሰፊ መርሐግብር ሁለት ዋና ዋና ዓላማዎችን ያነገበ ነው፤ አንደኛው በአቅምና በትራንስፖርት እጥረት ወደ አዲስ አበባ መምጣት ለማይችሉ የልብ ሕሙማን ባሉበት ክልል ድረስ ሄዶ ሕክምና መስጠት ሲሆን ሁለተኛው ከአዲስ አበባ ውጪ የሚገኙ የመንግሥት ሆስፒታሎችና ባለሙያዎች የልብ ሕክምና አገልግሎትን ራሳቸውን ችለው እንዲሰጡ የሥልጠና እና የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረግ ናቸው።
በዚህ በጎ ተግባር ላይ ለተሳተፉት የኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል፣ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል፣ እንዲሁም የጣልያኑ ቮቼ ፓድሪ ፒዮ እና CCPM አመራሮችና የሕክምና ባለሙያዎች በጅማ ዩኒቨርሲቲ አማካይነት የምስጋና እና የእውቅና መርሐግብር ተካሂዷል። በተለይም ከኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደረገው የጣልያን የሕክምና ባለሙያዎች ቡድን፣ ሥራውን አጠናቆ ጳጉሜን 2 ማምሻውን በክብር ወደ ሀገሩ ተሸኝቷል።
አቶ ብርሃን ተድላ ጨምረውም በአንድ ዓመት ውስጥ 1,000 የልብ ሕሙማን ሕፃናትን ለማዳን የተያዘው ግብ ከዳር እንዲደርስ፣ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ እንዲሁም የግልና የመንግሥት ተቋማት በገንዘብና በዓይነት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። አያይዘውም ለመርሐግብሩ ስኬት ድጋፍ ላደረጉ የጅማ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ የሕክምና ቡድን አባላት፣ እንዲሁም ለዳርክ ብሉ ኮንስትራክሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን ሙሉአለምና ባልደረቦቻቸው ላቅ ያለ ምስጋናቸውን በማቅረብ፤ ለመላው ኢትዮጵያውያን የሰላም፣ የጤና እና የእድገት አዲስ ዓመት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

27 days ago