Logo
SeledaPost
የአሜሪካ ፍርድ ቤት ለኢትዮጵያ እና ለሌሎች ሀገራት የዲቪ-2026 አመልካቾች ተስፋ ሰጪ ውሳኔ አስተላለፈ

የካሊፎርኒያ ክልላዊ ፍርድ ቤት ዳኛ ኤድዋርድ ዳቪላ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚስቴር በዲቪ አመልካቾች ላይ ተጥለው የነበሩ የቪዛ እገዳዎችን የሚያነሳ ውሳኔ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ የ48 ሀገራት አመልካቾች የቪዛ ሂደታቸውን እንዲቀጥሉ መንገድ መከፈቱ ተገለጸ።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚስቴር ቀደም ሲል ጥሎት የነበረውን እገዳ ያነሳ መሆኑን ያረጋገጠ ሲሆን፣ አመልካቾች እስከ መስከረም 20 ቀን 2019 ዓ.ም በሚጠናቀቀው የዲቪ-2026 ፕሮግራም ገደብ ውስጥ ሰነዶቻቸውን ማቅረብ እና የተያዙላቸውን ቃለ-መጠይቆች መከታተል እንደሚችሉ አስታውቋል።

ይህ የፍርድ ቤት ውሳኔ ለአፍሪካ ሀገራት ትልቅ እድል ይዞ የመጣ ሲሆን፣ ከ49 የአፍሪካ ሀገራት የተመረጡ እና ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ 53 ሺህ 939 ሰዎች በDV-2026 ተመዝግበው ይገኛሉ።

ከእነዚህ መካከል ግብፅ በ5,527 ከፍተኛውን ቁጥር ስትይዝ፣ አልጄሪያ በ5,457፣ ሱዳን በ5,226፣ ኬንያ በ3,949 እንዲሁም ኢትዮጵያ በ3,287 አመልካቾች ቀጣዩን ደረጃ በመጠበቅ ላይ ይገኛሉ።

ባለፉት አምስት ዓመታት ከ50 ሺህ በላይ ስደተኞችን ወደ አሜሪካ የላኩ እንደ ናይጄሪያ፣ ህንድ፣ ቻይና፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ ያሉ ሀገራት በዚህ ፕሮግራም ውስጥ አልተካተቱም።

በአለም አቀፍ ደረጃ ከ20.8 ሚሊዮን በላይ ብቁ ተወዳዳሪዎች መካከል 129,516 ሰዎች ለዲቪ-2026 የተመረጡ ሲሆን፣ ፕሮግራሙ በየዓመቱ እስከ 55 ሺህ ለሚደርሱ ዜጎች የአሜሪካ ቋሚ መኖሪያ ቪዛ ይሰጣል።

Seledadotio
Seledadotio
1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.