«የእናቴ ሮሚዮ» መጽሐፍ በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም ተመረቀ!
#fastmereja :- የጋዜጠኛና ደራሲ ስመኝ ግዛው አዲስ «የእናቴ ሮሚዮ» የተሰኘ አጭር ልቦለዶችን ያቀፈ መጽሐፍ ታዋቂ የሥነ-ጽሑፍ ባለሙያዎች፣ ምሁራን፣ አርቲስቶችና በርካታ አንባቢያን በተገኙበት በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም በድምቀት ተመረቀ።
መጽሐፉ ከምርቃቱ ቀደም ብሎ ለአንባቢያን የቀረበ ሲሆን ይህም አንባቢያን ያዩትን የተሰማቸዉን በነፃነት እንዲገልፁ እና ገንቢ አስተያየት እንዲሰጡበት ታስቦ ሲሆን፣ በዕለቱ በሥራው ጥበባዊ ይዘት እና የቴክኒክ ጥራት ላይ ጥልቅ ሂስና ዳሰሳ ቀርቧል።
የመጽሐፉን ዳሰሳ ያቀረቡት ረዳት ፕሮፌሰር መኩሪያ መካሻ እንደገለጹት፣ «የእናቴ ሮሚዮ» አንባቢን አጥብቆ የመያዝ እና ከፍተኛ ምስል ከሳችነት ያለው ጥበብ የተላበሰ ድንቅ ሥራ ነው፡፡
በምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የኪነ-ጥበብ ት ትዕይንቶች የቀረቡ ሲሆን፣ ከመጽሐፉ የተወሰደው «የሳቄ ኦዲተር» የተሰኘው ድርሰት ተዘጋጅቶ በመድረክ ተውኔት መልክ ቀርቧል። በተጨማሪም አንጋፋው ድምጻዊ ጌታቸው ጋዲሳ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ማርች ባንድ በመድረኩ ላይ በመገኘት ዝግጅቱን አደምቀውታል።
ጋዜጠኛና ደራሲ ስመኝ ግዛው በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባደረገችው ንግግር፣ መጽሐፉን ለመጻፍ ባሳለፈችበት ወቅት የነበረባትን ከባድ የጤና እክል አልፋ ለዚህ በመብቃቷ እግዚአብሔርን አመስግናለች።
ደራሲ ስመኝ አክላም በመጽሐፉ ውስጥ የትዳርና የቤተሰብ ሕይወት ተቋማዊ እሴቶችን ለመጠበቅና እውነተኛ ታሪኮችን ለማቅረብ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረጓን ገልጻለች።

1 month ago