Logo
FastMereja
የሰብል ምርቶችንና የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ለዓለም አቀፍ ገበያ የሚያስተዋውቀው ኤክስፖ ይፋ ሆነ!
#fastmereja :-የኢትዮጵያ ሰብል አምራቾች እና ላኪዎች ዘርፈ-ብዙ ማህበር ከኖርዲክ ትሬዲንግ (Nordic Trading PLC) ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት "1ኛው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ሰብል አምራቾች እና ኤግሪ-ቢዝነስ ኤክስፖ 2026" ሊካሄድ መሆኑ በዛሬዉ እለት በማርዮት ሆቴል በተካሄደ መርሀ-ግብር ተገልጿል።

በኢትዮጵያ የግብርና ታሪክ ትልቁ ዓለም አቀፍ የንግድና የቴክኖሎጂ መድረክ እንደሆነ የተነገረለት ይህ ኤክስፖ፤ የሀገሪቱን የሰብል ምርቶች፣ የግብርና ማቀነባበር (Agro-processing) አቅም፣ የኤክስፖርት እድሎች፣ የግብርና ቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን እና የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለዓለም አቀፍ ገበያ ለማስተዋወቅ መሆኑ ተገልጿል።

ከጥቅምት 16 ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በኮንቬንሽን ማዕከል በሚካሄደው በዚህ ታላቅ ኤክስፖ ላይ የሀገር ውስጥና የውጭ የሰብል አምራቾች፣ ላኪዎች፣ ምርት አቀባባዮች፣ ዓለም አቀፍ ገዢዎች፣ የግብርና ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የልማት አጋሮች እና የፖሊሲ አውጪዎች በስፋት ይሳተፋሉ።

ኤክስፖው ለአገር ውስጥ አምራቾች የቀጥታ የገበያ ትስስር (Strategic Market Linkages)፣ የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር እንዲሁም አወዳዳሪነትን የሚያሳድጉ የእሴት መጨመር እድሎችን የሚፈጥር መሆኑ ነዉ የተገለፀዉ።

ከዚህም በተጨማሪ በሀገር ደረጃ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ፣ የኢንቨስትመንት ፍሰትን ለመሳብ፣ የገበሬዎችን ገቢ ለማሻሻልና የስራ እድል ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተገልጿል።

በመጨረሻም በዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶች፣ አምራቾች፣ ላኪዎች፣ የፋይናንስና የኢንሹራንስ ተቋማት በኤክስፖው ላይ በመሳተፍ ይህንን አህጉራዊና ዓለም አቀፍ እድል እንዲጠቀሙበት ጥሪ አቅርበዋል።

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.