Logo
FastMereja
የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪ አሽከርካሪዎች ቻርጅ በሚያደርጉበት ወቅት የሥነ-ልቦና ድጋፍ የሚያገኙበት አዲስ አሰራር ተዘረጋ!
#fastmereja :-ግሪን ማይንድ ኔክሰስ (Green Mind Nexus) ከማይንድ ዘ ማይንድ(Mind the Mind / Five Gates Group) ጋር በመተባበር በአእምሮ ጤና፣ በአረንጓዴ ትራንስፖርት እና በወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ያተኮረ አዲስ ፕሮጀክት በዛሬዉ እለት ይፋ አድርጓል።

"ሰላም ለአሽከርካሪው፣ ሥራ ለወጣቱ፣ ስምምነት ለመንገዳችን" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚህ መድረክ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተመረጡ "Elite 30" ተማሪዎች የሁለት ወራት የሥልጠና እና የመስክ ምርምር ፕሮግራማቸውን በስኬት አጠናቀው የሰርተፊኬት ባለቤት መሆናቸዉ ተገልጿል።

ሰልጣኞቹ ባለፉት ሁለት ወራት ከ150 በላይ የኤሌክትሪክ መኪና አሽከርካሪዎች ጋር በመሆን የችግሮቻቸውን መንስኤ ያሰሰ ምርምር ያካሄዱ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የሥራና የኢንተርንሺፕ እድሎችን የማመቻቸት ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ነዉ የተገለፀዉ።

ፕሮጀክቱ ትኩረቱን በኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች (EV) ላይ በማድረግ የአየር ብክለትን ከመቀነስ ባለፈ፣ አሽከርካሪዎች መኪናቸውን በሚያሳፍኑበት (ቻርጅ በሚያደርጉበት) ወቅት ከ30 እስከ 40 ደቂቃ ባለው ጊዜ ውስጥ የሥነ-ልቦና ድጋፍ የሚያገኙበትን "Harmony Road" እና "Coffee & Harmony" የተሰኙ የሥነ-ልቦና የመጀመሪያ እርዳታ (Psychological First Aid) ፕሮግራሞችን መያዙ ነዉ የተገለፀዉ።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቁጥር ወደ 200,000 እየተጠጋ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህንን አገራዊ የኢነርጂ ሽግግር ለመደገፍ የባንኮች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተጠቁሟል።

ባንኮች ብድር በሚሰጡበት ወቅት ከንግድና ከገንዘብ ፍሰት ስሌት በተጨማሪ የአካባቢና ማህበረሰብ ተጽዕኖ ስጋት ምዘናን (Environmental & Social Risk Assessment) መተግበር እንዳለባቸውና ለዚህም የብሔራዊ ባንክ አስገዳጅ መመሪያዎች መውጣት እንደሚገባቸው ጥሪ ቀርቧል።

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.