Logo
Getu Temesgen
ለሚወዳት ሚስቱ ከሞት ጋር ትግል የገጠመው የፍቅር ሰው
#ethiopia | ​በሜክሲኮ ቬራክሩዝ ግዛት በሚገኘው ፖዛ ሪካ መንደር የካዞነስ ወንዝ ሞልቶ ድንገተኛ ጎርፍ በመፍጠሩ የተነሳ ሂላሪዮ ሬይኖሳ እና ባለቤቱ ኤሎዲያ ከባድ የህይወትና የሞት ፍልሚያ ውስጥ ገብተው ነበር።

ሂላሪዮ ከጠንካራ የውሃ ሞገድ ጋር መታገልን በደንብ የሚያውቅ የረጅም ጊዜ አሳ አጥማጅ ቢሆንም ባለቤቱ ኤሎዲያ ግን ዋና መዋኘት የማትችል በመሆኗ ሁኔታውን የበለጠ አደገኛ አድርጎት ነበር።

​የጎርፍ ማዕበሉ ኤሎዲያን በሃይል ጠራርጎ በወሰዳት ወቅት ሂላሪዮ ሳያወላውል ወደ አስፈሪውና ጭቃማው ውሃ ውስጥ ዘሎ በመግባት ፍለጋውን ተያያዘው።

በመጨረሻም ባለቤቱን አግኝቶ ኤሎዲያ አንገቱ ላይ አጥብቃ እንድትደገፈው በማድረግ ያንን ሁሉ ኃይለኛ የጎርፍ ማዕበል በጥንካሬ ሰንጥቆ በመዋኘት ህይወቷን ታደገ።

​ምንም እንኳን መኖሪያ ቤታቸው ሙሉ በሙሉ በውሃ የተዋጠ ቢሆንም ባልና ሚስቱ የጎርፍ ውሃው በከበባቸው ሁኔታ ውስጥ ለሰዓታት ያህል እርስ በእርስ ተደጋገፎ በመቆየት ህይወታቸውን ማዳን ችለዋል።

ይህ አጋጣሚ በአደጋና በውሃ ማዕበል መሃል ከአሰቃቂው የጎርፍ ኃይል ይልቅ አንድ ባል የሚወዳትን ባለቤቱን ለማዳን የነበረው ቆራጥነትና እውነተኛ ፍቅር ምን ያህል ጠንካራ እንደሆነ በተግባር ያሳየ ነበር።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.