በዓለም መድረኮች የአፍሪካን ድምጽ የምታጎላው ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በታሪኳ ሙሉ ሉዓላዊነቷን አስከብራ የኖረች የነፃነት ምልክት ብቻ ሳትሆን፤ የመላው አፍሪካውያን ድምፅ በዓለም አቀፍ መድረክ ጎልቶ እንዲሰማ የቀዳሚነትን ሚና ስትጫወት የኖረች የአህጉሩ የዲፕሎማሲ ማዕከል ናት።
ከተባበሩት መንግሥታት ጉባኤዎች እስከ ብሪክስ እንዲሁም በበርካታ የዓለም መድረኮች ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እኩልነት፣ ነፃነትና ልማት በፅናት የምትቆረቆርና የምትሞግት ሀገር ነች፡፡
ኢትዮጵያ የቀድሞውን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት፤ የአሁኑን የአፍሪካ ህብረት በመመስረት ሂደት መሃንዲስ በመሆን የነበራት ሚና ታሪካዊ ነው።
የኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ዋና ከተማ በመሆን የአህጉሪቱ ሀገራት በአንድ ጥላ ስር እንዲሰበሰቡ አድርጋለች።
በቅኝ ግዛት ስር የነበሩ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ነፃነታቸውን እንዲጎናፀፉ የገንዘብ፣ የዲፕሎማሲና የሎጂስቲክስ ድጋፍ በማድረግ የአህጉሪቱን ነፃነት ያረጋገጠች ቀንዲል፤ የጽናት ተምሳሌት ናት።
በዓለም አቀፍ መድረኮች የአፍሪካ ድምፅ የማይሰማበትና ፍትሃዊ ያልሆኑትን ዓለም አቀፍ አካሄድን ለመቀየር በግንባር ቀደምትነት እየተሟገተች፤ መፍትሄ እንዲሰጥ በማሳመን ዘልቃለች።
በተለይም አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ቋሚ ውክልና እንዲኖራት ጠንካራ የዲፕሎማሲ ትግል እያደረገች ትገኛለች።
በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች (ኮፕ) የበካይ ጋዝ ልቀት አነስተኛ በሆነባት ነገር ግን የጉዳቱ ሰለባ ለሆነችው አፍሪካ የካሳ እና የፋይናንስ ድጋፍ ጥያቄዎችን በፅናት በማቅረብ የአፍሪካን አቋም ስታንጸባርቅ ቆይታለች።
በተጨማሪም በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አማካኝነት የቀጣናውን ተፈጥሮ መልሶ የመንከባከብ ቁርጠኝነትን በተግባር በማሳየት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምሳሌ ሆናለች።
በአጠቃላይ ኢትዮጵያ እንደ ትናንቱ ዛሬም፤ ወደፊትም የምትቀጥለው የአፍሪካ ድምፅ፣ ጋሻና መሪ በመሆን ነው።
በዲፕሎማሲያዊ ከፍታዋና በጠንካራ የፓን አፍሪካኒዝም እምነቷ የአፍሪካን ክብርና ጥቅም በዓለም አቀፍ ደረጃ ማስከበሯን ትቀጥላለች።
በመልካም ፈቃዱ

1 month ago