Logo
EBC
ማንቸስተር ሲቲ ክሪስታል ፓላስን 4 ለ 1 አሸነፈ
******************

በ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር፣ ማንቸስተር ሲቲ ክሪስታል ፓላስን ገጥሞ 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል።

በሴልኸርስት ፓርኩ ጨዋታ ለማንቸስተር ሲቲ የማሸነፊያ ግቦቹን ኤርሊንግ ሃላንድ በ17ኛው እና 84ኛው ደቂቃ ላይ እንዲሁም ራያን ቸርኪ በ54ኛው እና 59ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፈዋል።

ክሪስታል ፓላስ ብቸኛዋን ግብ ያገኘው በ56ኛው ደቂቃ ላይ ዶናሩማ በራሱ መረብ ላይ ባስቆጠረው ኳስ ነው።

በጨዋታው ማንቸስተር ሲቲ ሁለተኛ ተከታታይ ድሉን ማስመዝገቡን ተከትሎ ነጥቡን ስድስት በማድረስ ሌሎች ቡድኖች እስኪጫወቱ ድረስ ሊጉን መምራት ጀምሯል።
#manchestercityfc #crystalpalace #epl #premierleague #football #sports #ebc Ethiopian Broadcasting Corporation

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.