የመደመር አንቀጽ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ራዕይ ብልጽግናን ማረጋገጥ ነው። ከትናንት ወረት ቆጥረን ዛሬን በትጋትና ጥበብ ሠርተን ለትውልድ የበለጸገ ሀገር የማሻገር ራዕይን ሰንቀናል።ራእያችንን ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲጋሩን እንፈልጋለን።
በዚህ ራዕይ ውስጥ የኢትዮጵያዊ ማኅፀን ያፈራው ሁሉ ራሱን ሊመለከትበት ይገባል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን በከፋ ጭቆና፣ በተደጋገመ ገርነት፣ በአሰቃቂ ረሃብ፣ አንገት በሚያስደፋ ስደትና ጉስቁልና ውስጥ አልፈናል።
መከራና ችግር እንደዶፍ ቢወርድብንም፣ የድህነት ሐሩር እንደሰም አቅልጦ እንደጧፍ ቢያነደንም፣ ላንረታና ሳንበተን በብርታት ዛሬ ላይ ደርሰናል። በፈተና ውስጥ ያበረታን ወረታችን ነው። ዐርበኝነትና መንፈሳዊነት ታላላቅ ወረቶቻችን ናቸው።
ዛሬ እነዚህን አንጡራ ወረቶቻችንን ይዘን፣ ጉልበታችንን ያዛለውን ድህነትን አራግፈን፣ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ ራዕይ ሰንቀናል።
የመደመር መንግስት
ገጽ - 295
Ethiopian Broadcasting Corporation #ebc #ethiopia #ebcdotstream #medemer

1 month ago